የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በጊብሰን ትምህርት ቤት የሚማሩ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎችን ከተማ አቀፉን የሚኒስትሪ ፈተና ትምህርት ቤቱ ማስፈተን እንደማይችል እንዳሳወቀው ት/ቤቱ ገልጿል።

ጊብሰን ትምህርት ቤት ” ባጠፋቸው ጥፋቶች ምክንያት እግድ ስለተጣለበት ተማሪዎችን ማስፈተን አይችልም ” የተባለ ሲሆን ትምህርት ቢሮው ተማሪዎችን ሌላ ትምህርት ቤት ወስዶ በማስፈተን የሚኒስትሪ ካርዱ ላይም ” በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ስር ” የሚል እንደሚፃፍበት ተገልጿል።

ይህን ውሳኔ ወላጆች እንደማይቀበሉት ገልጸዋል።

ወላጆች ምን አሉ ?

– ልጆቻችን በተማሩበት ት/ቤት ስር ነው መፈተን ያለባቸው

– የተነገርን ነገር የለም

– ባለቀ ሰዓት ነው ይህን የሰማነው

– በተቀመጠው ካሪኩለም እንደሚማሩ ነው እኛ የምናውቀው

– ልጆቻን ካሪኩለሙ የሚፈቅደውን ነው የሚማሩት

– ቋንቋ ችግር አለ ወይ ? የለም

– ሌሎች ት/ቤት የሚተገበረው ነው እዚህም ያለው

– ከሌሎች የመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚለየው ሳይንስ እና ሂሳብን በተጨማሪ እንግሊዘኛ ቋንቋ ያንኑ ካሪኩለም ጠብቆ ማስተማሩ ነው። እኛ ትምህርት ቤቱን የመረጥነው ተጨማሪ ቋንቋ ስለሚያስተምር ነው።

– በተቀመጠው አማራጭ ሁለት ቋንቋ እያስተማረ ነው። አፋን ኦሮሞ እና አማርኛ በትምህርት አይነት ደረጃ እየተማሩ ነው። የቀረ ነገር የለም።

– በመደበኛው ፕሮግራም ምንም የተጣሰ ነገር የለም።

የአዲስ አበባ ከተማ የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ አድማሱ ደቻሳ ትምህርት ቤቱ ብዙ ጥሰት ፈጽሟል ብለዋል።

አቶ አድማሱ ደቻሳ ምን አሉ ?

° የትምህርት አይነት ጨምሮ ማስተማር

° የክፍለ ጊዜ ጥሰት

° የትምህርት ቋንቋ አለማክበር

° የአፍ መፍቻ ቋንቋ የሀገራችን ” እንግሊዘኛ ነው ” ብሎ ስታንዳርድ እስከመያዝ መድረስ፤

° በእንግሊዝኛ አፋቸውን የፈቱ ካሉ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት አለ እዛ መማር ይችላሉ ግን በከተማው ፍቃድ የወሰደ ት/ቤት ” የአፍ መፍቻ ቋንቋው እንግሊዝኛ ነው ” በሚል ማስተማር አይችልም።

° የሀገር በቀል ቋንቋ ጠል መሆን ተገቢ አይደለም።

° ተጨማሪ ቋንቋ በጥናት የተመለሰ ነው ይህንም እንዲታወቅ ብዙ ተሰርቷል ይህ ሆኖ እያለ ‘ አናውቅም፣ አልሰማንም ፣የሚመጣ ነገር የለም ‘ የማለት ነገር አለ።

አንድ ወር ለቀረው የትምህርት ጊዜ ይህን ውሳኔ ለምን አሳለፋችሁ ? ለምን አልታገሳችሁም ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ፦

አቶ አድማሱ ደቻሳ ፦

” እኛ እልህ እየተጋባን አይደለም። የተወሰደው እርምጃ ከ4 ወር በፊት ነው። ነገር ግን ት/ቤቱ ተማሪና ወላጆችን መጠቀሚያ ለማድረግ ጥረት አድርጓል። እርምጃው ከተወሰደ ግን ቆይቷል።

ከፈተና ጋር ተያይዞ ግልጽ ነው አንድ የትህምህርት ተቋም እውቅና ፍቃድ ኖሮት ወደ ፈተና ስርዓት ሲገባ ኮድ ይሰጠዋል ይህ የትምህርት ተቋም የእውቅና ፍቃዱ ቀድሞ የተነሳ ስለሆነ ኮድ ሊሰጠው አይችልም።

ኮድ ባልተሰጠበት ትምህርት ተቋም ተማሪዎች ይፈተኑ ቢባል ፈተናቸው ሊታረም አይችልም።

ስለዚህ ኮድ ወዳለው ትምህርት ተቋም ወስደን ነው የምናስፈትናቸው።  ” ሲሉ መልሰዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 መሆኑን ይገልጻል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ (@tikvahethiopia  )