“የዩኒቨርስቲ ቆይታዬ የመጨረሻ ትውስታ የተማሪዎች መታሰር ነው”

ባለፉት ሳምንታት በአሜሪካ 130 ኮሌጆች ውስጥ የፍልስጤም ደጋፊዎች ሰለማዊ ሰልፍ ወጥተዋል።

ተማሪዎቹ ዩኒቨርስቲዎቻቸው ከእስራኤል ጋር ትስስር ካላቸው ተቋማት ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲያቆሙ ጠይቀዋል።

በተደጋጋሚ የተሰጣቸውን ማስጠንቀቂያ ጥሰው በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ድንኳን ጥለው ለቀናት ተቃውሟቸውን ቀጥለዋል።

ፖሊሶች ተቃውሞውን በትነው ከ2,000 በላይ ሰዎች አስረዋል። ቢቢሲ ሦስት ተመራቂ ተማሪዎችን ስለ ተቃውሞው አነጋግሯል።

‘የመጨረሻ ትውስታዬ ተማሪዎች በፖሊስ ሲጎተቱ ማየት ነው’

ማዲሰን ሞሪስ 22 ዓመቷ ነው። የቴክሳስ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ናት። ትውስታዋን እንዲህ ትገልጻለች። ፖሊሶች ዩኒቨርስቲ ውስጥ የገበቡበት ቀን የመጨረሻ ፈተናዬን የምወስድበት ዕለት ነበር።

ዩኒቨርስቲ ስደርስ ፖሊሶች ተማሪዎችን ከበዋል።በጣም አስጨናቂ ነበር። በዚህ ሁሉ ፖሊስ ተከብበቤ አላውቅም። ያስፈራል።

ለፈተናዬ ማጥናት አልቻልኩም። ትኩረቴን መሰብሰብ ተሳነኝ።

ይሄ ስሜት እስከወዲያኛው ድረስ ከአእምሮዬ አይወጣም። የዩኒቨርስቲ ቆይታዬ የመጨረሻ ትውስታ ይሄ ነው። ይሄን ሁሉ አሉታዊ ነገር እያዩ ደስተኛ መሆን ራሱ አይቻልም።

በስኬቴ ደስተኛ መሆን አልቻልኩም። ቀጥሎ ምርቃት ይመጣል።ለአራት ዓመታት ስጠብቀው ነበር። በኮቪድ ምክንያት ከሁለተኛ ደረጃ መመረቅ አልቻልንም ነበር።

የመጨረሻ ዓመቴን በደንብ ለማጣጣም ስሞክር ነበር። ግን እየሆነ ያለው ነገር አሳዛኝ ነው።

‘ምርቃቴ ዕውን ላይሆን ይችላል’

ክሬግ ብሪክሄድ 21 ዓመቱ ነው። በዬል ዩኒቨርስቲ ይማራል። ያሳለፈውን እንዲህ ይገልጻል። ታስረው ከነበሩት 48 ተማሪዎች መካከል አንዱ ነኝ።

ፖሊሶች የዩኒቨርስቲው ጊቢ ውስጥ ገቡና አሰሩን። በጣም አስጨናቂ ጊዜ ነው ያሳለፍነው።ሁለት የመመረቂያ ጽሑፎች ይቀሩኛል። እየሆነ ባለው ነገር ምክንያት ግን ማጠናቀቅ አልቻልኩም።

የመጨረሻ ዓመት ትምህርት በጣም ዋጋ አለው። ቤተሶቼንም አስባለሁ። ስመረቅ ማየት ይፈልጋሉ። ግን መመረቅ ላንችል እንችላለን።

ዲፕሎማችን ላይሰጠን ይችላል። ይሄ ከሌለ ደግሞ ሁለተኛ ዲግሪ መቀጠል አንችልም።

በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ሁለተኛ ዲግሪዬን መቀጠል አስቤ ነበር።

በፍልስጤም ያለው ሁኔታ ተቀባይነት የለውም።

ኮቪድ ሲመጣ ሁሉም ነገር ቆሞ ወደቤት እንድንሄድ ነበር የተነገረን።

ከዚያ ‘ብላክ ላይቭስ ማተር’ ተቃውሞ ተነሳ። እነዚህ ናቸው አሁን ላለሁበት ማንነት ዋጋ ያላቸው።

‘ተቃዋሚዎቹ የተማሪዎቹን ሕይወት አሰናከሉ’

መሊሳ ማናሽ 21 ዓመቷ ነው። የሳውዘርን ካሊፎርንያ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ናት። ታሪኳን እንዲህ አካፍላለች።ወቅቱ የደስታ መሆን ነበረበት። ግን ያለፉት ቀናት ከባድ ሆኑ።

እየሆነ ያለው ነገር ይረብሻል። ቀውስ ነው የተፈጠረው።ተቃዋሚዎቹ የተማሪዎችን ሕይወት እያመሳቀሉ ነው። ቤተ መጻሕፍት እስካሁን አልተከፈተም።ብዙዎች ለመጨረሻ ፈተና እየተዘጋጁ ነው። ግን በላያችን ላይ ሄሊኮፕተር እያንዣበበ ነበር።

ሁለት የዩኒቨርስቲው በሮች ብቻ ናቸው የተከፈቱት። ስለዚህ ረዥም ርቀት እየሄድነ ነው የምንገባው። ተቃዋሚዎች የዩኒቨርስቲውን መንገድ ስለፈሩ መንቀሳቀስ ያስፈራል።

አብዛኞቹ አይሑዳውያን ተማሪዎች ፈርተናል። ይጮሁብናል። የዘር ጭፍጨፋ ደጋፊ ይሉናል። በጣም አስቀያሚ ነገር ነው የሚሉት።

ይሄ ሁሉ ፊት ለፊታችን እየሆነ ስለነገሩ አለማሰብ አይቻልም። ምርቃት ይቀራል ቢሉኝ አላምንም ነበር። መቅረቱን ስንሰማ በጣም አዘንን።

ይሄ በትምህርት ሕይወታችን ትልቅ ቦታ ያለው ነው። ስንጠብቀው የነበረ ነገር ቀረ። በኮቪድ ምክንያት ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርትም ሳንመረቅ ነው የቀረነው::

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ ( ቢቢሲ ዜና )