ፍልስጤማውያን ከራፋሕ የተወሰኑ አካባቢዎች እንዲወጡ እስራኤል አስጠነቀቀች

የእስራኤል መከላከያ ፍልስጤማውያን ከምሥራቃዊ ራፋሕ እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ መስጠት መጀመሩን አስታወቀ።

ማስጠንቀቂያ መስጠት የጀመረው በደቡባዊ ጋዛ ከሚያደርገው “የተወሰነ” ኦፕሬሽን በፊት እንደሆነ ገልጿል።

ወደ 100,000 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በካሀን ዩኑስ እና አል-ማዋሲ ባሉ “ሰብአዊ ሥፍራዎች” እንዲሄዱ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።

ጦርነቱ ሰባት ወራት የሆነው ሲሆን፣ እስራኤል ሐማስን ለማሸነፍ ራፋሕን መውሰድ እንዳለባት ገልጻለች።

የተባበሩት መንግሥታት እና አሜሪካ ግን ከሦስት ሚሊዮን በላይ ተፈናቃይ ፍልስጤማውያን በሚኖሩበት ራፋሕ ከተማ ላይ የሚፈጸም ጥቃት ከፍተኛ ቀውስ እንደሚያስከትል አሳስበዋል።

ከፍተኛ የሐማስ ባለሥልጣን የወጣውን ማስጠንቀቂያ “አደገኛ የነገሮች መጋጋል” ሲሉ ገልጸውታል።

በራፋሕ የእስራኤል አየር ጥቃት በአንድ ምሽት ቢያንስ 19 ፍልስጤማውያንን እንደገደለ ሪፖርት ተደርጓል።

ከሪም ሻሎም በተባለና ወደ ጋዛ ዋነኛው የእርዳታ ማስገቢያ በሆነው አካባቢ የሐማስ ተዋጊዎች አራት የእስራኤል ወታደሮችን ከገደሉበት ቦታ በተተኮሰ ሮኬት ነው ይህ ጉዳት የደረሰው።

ይህ ጥቃት የተፈጸመው አዲስ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ ጥረት እየተደረገ ባለበት ወቅት ነው። አሸማጋዮች ጥረታቸውን ቀጥለዋል።

የእስራኤል መከላከለያ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ሌተናንት ኮሎኔል ናዳቭ ሾሻኒ እንዳሉት በራፋሕ የሚካሄደው ኦፕሬሽን “ውስን ስፋት ያለው” ነው።

ቀነ ገደብ እንዳልተቀመጠና ነዋሪዎችን የማስወጣት ሂደት ቀስ በቀስ እንደሚካሄድ አክለዋል።

ነዋሪዎች እንዲወጡ በአጭር የጽሑፍ መልዕክት፣ በበራሪ ወረቀትና በማኅበራዊ ሚዲያ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠ ነው።

ፍልስጤማውያን እንዲሄዱበት የተጠየቁት ቦታ ሰብአዊ መጠለያ ሥፍራ እንደሆነና ሆስፒታል፣ ምግብና መጠጥ እንዲሁም አስፈላጊ ነገሮች እንደሚገኙበት የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ገልጿል።

መሬት ላይ ያለውን ሁኔታ በመከተል ሰዎች እንዴት እንደሚንቀሳቀሱ ማሳሰቢያ እንደሚሰጥም ያክላል።

ጠቅላይ ሚኒስተር ቤንያሚን ኔታንያሁ፣ ላለፉት ወራት ሐማስን ማሸነፍ የሚቻለው በሙሉ ጦርነት ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

አራት የሐማስ ባታሊዮን በራፋሕ እንዳለ እስራኤል ትገልጻለች። በዚህም በሺዎች የሚቆጠሩ ተዋጊዎች እንዳሉ አስታውቃለች።

በእስራኤል ጥቃት ከ32,490 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የጋዛ ጤና ሚኒስትር አስታውቋል።

የምዕራቡ አረብ አገራት ኅብረቶችና የተባበሩት መንግሥታት በራፋሕ ወረራ ሊኖር እንደሚችል በተደጋጋሚ አስጠንቅቀዋል።

በተባበሩት መንግሥታት የፍልስጤማውያን ስደተኞች ጉዳይ የሚከታተለው ክፍል ሊደርስ የሚችለው ጉዳት “ለ1.4 ሚሊዮን ሰዎች የከፋ ነው” ሲል አሳስቧል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ ( ቢቢሲ ዜና )