” የስፖርት ውርርድ / የቤቲንግ ቤቶች #ሊታገዱ ይገባል ” ሲል የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር አሳሰበ።

ሚኒስቴሩ ዛሬ የ9 ወር የስራ አፈጻጸም ሪፖርቱን ለተ/ም/ቤት አቅርቦ ነበር።

በዚህ ወቅት ፤ ” የወጣቶች ሱሰኝነት በሀገር ደረጃ እየተባባሰ መጥቷል ፤ በተለይ አሉታዊ መጤ ልማዶች እና አደንዛዥ ዕጽ እንደ ሀገር እየተስፋፋ መጥቷል ” ሲል ገልጿል።

ይህም ብዙ ወጣቶችን እያሳጣን ነው ሲል አስረድቷል።

ወጣቶች ሰብዕና ግንባታ ላይ ተግዳሮት እየፈጠረ ከሚገኘው አንዱ የስፖርት ውርርድ እንደሆነ ያመለከተው ሚኒስቴሩ ” የስፖርት ውርርድ ለሀገሪቱ ከሚያስገባው ገቢ አኳያ ብቻ መታየት የለበትም ” ብሏል።

” ‘ ስፖርት ቤቲንግ ‘ ላይ ያሉት፣ ካሁን በፊት የወጡት መመሪያዎች፣ ደንቦች፤ ጥናትን መሰረት አድርገው ሊታገዱ ይገባል ” ሲል ገልጿል።

ፓርላማውም በዚህ ረገድ እገዛ ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስቧል።

” ገቢ አንድ ነገር ነው። ሀገር ገቢ ማግኘት አለባት ” ያለው መ/ቤቱ ነገር ግን ፦

➡️ በወጣቶቹ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያስከተለ ስለሆነ፣

➡️ ብዙ ወጣቶች እያሳጣ ስለሆነ፣

➡️ ብዙ ቤተሰብም #እየፈረሰ ስለሆነ ሊታገድ እንደሚገባ ገልጿል።

በህ/ተ/ም/ቤት የጤና ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ፤ ” ብሔራዊ ሎተሪ ከገቢ ጋር አይቶታል። በዚህም በኩል ደግሞ ሌላ ችግር እየፈጠረ ነው ” ያለ ሲሆን ” ተማሪዎች ዩኒፎርማቸውን እያወለቁ የስፖርት ውርርድ ቤት ይገባሉ። ስለዚህ መቼ ያጥኑ። አእምሮአቸው ሊጎዳ ስለሚችል ጥንቃቄ ተደርጎ መሰራት አለበት ” ብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በስፖርት ውርርድ ላይ በተሰማሩ አገልግሎት ሰጪዎች ላይ በቅርቡ የወሰደውን እርምጃ ” ጥሩ ስራ ” ሲል አወድሷል።

በሌሎች አካባቢዎች በተሞክሮ ሊወሰድ ይገባል ሲል ጠቁሟል።

የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴርም ፤ ከስፖርት ውርርድ ጋር በተያያዘ ያለውን የወጣቶች ሁኔታ የወደፊት የትኩረት አቅጣጫ አድርጎ እንዲያየው እና ጠንካራ ክትትል እንዲያደርግ መክሯል።

ከዚህ ቀደምም የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር የስፖርት ውርርድ / ቤቲንግ / ‘ #ቁማር ‘ ነው ብሎ እንደሚያምን ገልጾ እንዲታገድ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ግን ፤ ” ቤቲንግ ” ‘ #ጨዋታ ‘ እንጂ ‘ ቁማር ‘ ነው ብሎ እንደማያምን ገልጾ ነበር። ቤቲንግ አትራፊና ብዙ ወጣቶች ስራ እንዲያገኙ ያደረገና በከፍተኛ ሁኔታ ገንዘብ እንዲንቀሳቀስ የሚያደርግ መሆኑንም አስረድቶ ነበር።

በስርዓት እንዲመራም መመሪያዎች ወጥተውለት እየተሰራ መሆኑን በመግለጽ ” እኛ ጨዋታውን አቅርበናል ተጫዋቹ ደግሞ በኃላፊነት መጫወት አለበት ” ሲል ነበር የመለሰው።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ ( @tikvahethiopia )