ባይደን ፊርማቸውን አኑረዋል ፤ ቲክቶክ ” ፍርድ ቤት እንተያይ ” ብሏል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በባይት ዳንስ ባለቤትነት ያለው ” #ቲክቶክ ” ድርሻው ለአሜሪካ ኩባንያ ተሽጦ ከቻይና ካልተፋታ በመላው አሜሪካ #እንዲታገድ የቀረበላቸው ረቂቅ ሕግ ላይ ፊርማቸውን በማኖር ሕግ ሆኖ  እንዲወጣ አድርገዋል።

” ቲክቶክ ” ድርሻው ለአሜሪካ ኩባንያ እንዲሸጥ የተሰጠው ጊዜ ከ9 ወር እስከ 1 ዓመት ብቻ ነው።

በዚህ ጊዜ ይህንን ካላደረገ #እስከወዲያኛው ከአሜሪካ እንደሚታገድ ተገልጿል።

አሁን በአሜሪካ ብቻ 170 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ያሉት ” ቲክቶክ ” ሙሉ በሙሉ የመታገዱ ነገር #እውን ወደ መሆኑ ተቃርቧል።

የቲክቶክ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ሹ ዚ ቼው ፥ ” የትም አንሄድም። ለመብታችን በፍርድ ቤት እንታገላለን። ሀቁ እና ህገ መንግስቱ ከጎናችን ናቸው፣ እናሸንፋለን ብለን እንጠብቃለን ” ሲሉ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ፤ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለዩክሬን ፣ እስራኤል እና ታይዋን የቀረበው የ95 ቢሊዮን ዶላር የድጋፍ ጥቅል ረቂቅ ሕግ ላይ ፊርማቸውን አኑረዋል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ ( @tikvahethiopia )