” ሰዎቹ ናቸው አታልለውኝ እዚያ ድረስ የወሰዱኝ ” – ቀሲስ በላይ መኮንን

የቀሲስ በላይ መኮንን ጠበቃ አቶ ቱሊ ባይሳ ስለ ዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።

በዚህም ወቅት ፥ ደንበኛቸው ቀሲስ በላይ መኮንን በሐሰተኛ ሰነድ ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለማውጣት ሙከራ ተደርጎበታል የተባለው ቦታ የተገኙት ” ሰዎች አታልለዋቸው ” እንደሆነ ለፍ/ቤት መናገራቸውን ገልጸዋል።

ጠበቃ ቱሊ ፤ ” እሳቸው በቦታው ከመገኘት ውጪ ደብዳቤውን በማዘጋጀት፣ በመቀበል በዚህ ወንጀል ውስጥ ተሳትፎ የላቸውም ” ያሉ ሲሆን ” ደብዳቤው ላይ የእሳቸው ስም፣ የባንክ ቁጥር የለም። የቤተ ክርስቲያን የሂሳብ ቁጥር የለም ” ብለዋል።

” ከመጀመሪያውም ወንጀሉ በሌሎች ሰዎች የተሞከረ ቢሆንም እሳቸውን አይመለከትም ” ሲሉ ገልጸዋል።

በችሎቱ ላይ ለመናገር ዕድል ያገኙት ቀሲስ በላይ የአፍሪካ ኅብረት ቅጥር ግቢ ውስጥ የተገኙት ” ሰዎች ወስደዋቸው ” እና ” #ተታልለው ” እንደሆነ ተናግረዋል።

” በዚያ ቦታ ላይ ከመገኘት ውጪ ምንም የፈጸሙት ድርጊት እንደሌለ ” ገልጸዋል።

ቀሲስ በላይ ፦

” ሰዎቹ ናቸው አታልለውኝ እዚያ ድረስ የወሰዱኝ። እኔ ወደዚያ የሄድኩት ለመተባበር፣ ይህ ሰነድ ‘ትክክለኛ ሰነድ ነው አይደለም’ የሚለውን የባንክ ማናጀሮችን ለመጠየቅ ነው እንጂ በምንም ሁኔታ በሰነዱ ለመገልገል አስቤ አይደለም። ጉዳዩ ዞሮ እኔ ታሳሪ ሆንኩኝ እንጂ፤ ሰነዱ ‘ትክክል አይደለም’ የሚል የባንክ ማናጀሩ ሲገልጹልኝ ወዲያው ፖሊስ ያስጠራሁት እኔ ነኝ ” ማለታቸውን ጠበቃው ተናግረዋል።

ቀሲስ በላይ ሰነዱን አዘጋጅተዋል የተባሉ ሰዎች ” ማምለጣቸውን ” እንዲሁም ስለ ሰነዶቹ ” የሚያውቁት እና መመርመር ያላባቸው ” እነሱ እንደሆኑም ለፍርድ ቤቱ አንስተዋል ተብሏል።

በዛሬው የፍ/ ቤት ውሎ የቀረበው የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደርጎ ለመርማሪ ፖሊስ ስምንት ተጨማሪ ቀን መሰጠቱ ይታወቃል።

 

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ ( ቢቢሲ ዜና )

 

 

 

 

 

Show Buttons
Hide Buttons