“ ገዳሙ በከፍተኛ ችግር ላይ ይገኛል ” – አቡነ ሐራ ድንግል አንድነት ገዳም

አቡነ ሐራ ድንግል አንድነት ገዳም በዙራያው በሰፈሩ ሰዎች የታዘ መሬቱን ለማስመለስ የካሳ ክፍያ መጠየቁን አስታወቀ።

በአማራ ክልል የሚገኘው ገዳመ ወንያት አቡነ ሐራ ድንግል አንድነት ገዳም ከ30,000 እስከ 50,000 የሚሆኑ ፀበልተኞች እንደሚጸበሉበት ይሁን እንጂ የገዳሙ መሬት ሰዎች ስለሰፈሩበት እንኳን ለጸበልተኞች ለመነኮሳቱም እጅግ በመጣበቡ፣ “ ገዳሙ በከፍተኛ ችግር ላይ ይገኛል ” ተብሏል።

የገዳሙ ይዞታ የጠበበው ከበርካታ ዓመታት ጀምሮ ለመፈወስ ወደ ስፍራው የሚሄዱ ፈውስ ያገኙ ጸበልተኞችና አርሶአደሮች ከሕመማቸው ከተፈወሱ በኋላ በገዳሙ መሬት ቤት እየሰሩ እዚያው በመኖራቸው መሆኑን የገዳሙ መነኮሳት አስረድተዋል።

ሰዎቹ በአንዴ ሳይሆን ቀስ በቀስ እዛው መኖር እንደጀመሩ ጠቁሟል።

በገዳሙ ይዞታ የሰፈሩ ከ250 በላይ አባውራዎች ይነሱ ዘንድ ለጠየቁት ካሳና ለሌሎች አገልግሎቶች ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ አሳውቋል።

ለዚህም ሚያዚያ 19/2016 ዓ/ም በካፒታል ሆቴል የገቢ ማሰባሰብ መርሀ ግብር እንደተዘጋጀ፣ በመሆኑም በውስጥም በውጪ ያሉ ኢትዮጵያዊያን እርብርብ እንዲያደርጉ ገዳሙ ጥሪ አቅርቧል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ (@tikvahethiopia )