” የመኪና እቃ የተሰረቀባችሁ በአካል ቀርባችሁ ንብረታችሁን ምረጡ ” – ፖሊስ

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ በከተማይቱ የመኪና እቃ ስርቆት ወንጀል ስጋትን ለመቀነስ ሕግን መሰረት ያደረገ ኦፕሬሽን በልደታ ፤በአራዳ እና አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አዋሳኝ ወረዳዎች ላይ መስራቱን አሳውቋል።

ፖሊስ በተለምዶ ሱማሌ ተራ በሚባለው አካባቢ ባካሄደው ኦፕሬሽን ፦

➡ 528 ልዩ ልዩ ፍሬቻዎችን ፣

➡ 187 ስፖኪዮችን ፣

➡ 113 የመኪና መብራቶች ፣

➡ 172 የዝናብ መጥረጊያ በአጠቃላይ 33 ልዩ ልዩ በድምሩ 1 ሺ 269 አይነት የመኪና እቃዎችን መያዙን አስታውቋል፡፡

የተሰረቁ የመኪና እቃዎችን ሚገዙና የሚያሻሽጡ 89 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ መቀጠሉን ገልጿል።

በተለያየ ጊዜ የመኪና እቃ የተሰረቀባቸው ግለሰቦች ፦

° በልደታ ፣

° በአራዳ

° በአዲስ ከተማ ክ/ ከተማ ፖሊስ መምሪያዎች በመቅረብ  ንብረታቸውን መምረጥ እንደሚችሉም ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፥ በከተማው ለመኪና እቃ ስርቆት መስፋፋት ልዩ ልዩ ምክንያቶች ቢኖሩም በተለይ ወንጀለኞችን በማደራጀትና በማሰማራት የመኪና እቃ የሚያሰርቁ እና የተሰረቁ እቃዎችን የሚገዙ ህገ-ወጦች ለወንጀሉ መስፋፋት ዋና ምክንያት ናቸው ብሏል።

 

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ(@tikvahethiopia)