የአሜሪካ #ሴኔት በመላው አሜሪካ ” ቲክቶክ” ን ሊያግድ የሚችል አዋጅ ትላንት ለሊት አጽድቋል።

ከቀናት በፊት የተወካዮች ምክር ቤት ” ቲክቶክ ” እንዲታገድ ረቂቅ ሕግ ማጽደቁ ይታወሳል።

ትላንት ለሊት የአሜሪካ ሴኔት ተሰብስቦ ” ቲክቶክ ” ከቻይና ካልተፋትና ድርሻው በ9 ወር ውስጥ ለአሜሪካ ኩባንያ የማይሸጥ ከሆነ አሜሪካ ውስጥ አገልግሎት እንዳይሰጥ የሚያግድ አዋጅ አጽድቋል።

ቀጣዩ ሂደት ፕሬዜዳንቱን ይመለከታል።

ይህ አዋጅ ወደ ፕሬዝዳንት ጆ  ባይደን የተመራ ሲሆን እሳቸው ቀደም ሲል ” ይህ አዋጅ እኔ ጋር ይድረስ እንጂ ፊርማዬን አኑሬበት ሕግ ሆኖ ይተገበራል ” ብለው ነበር።

አሁን አሜሪካ ውስጥ 170 ሚሊዮ ተጠቃሚዎች ያሉት ” ቲክቶክ ” የመታገዱ ነገር እውን እየሆነ የመጣ ሲሆን ሂደቱ ረጅም ወራትን ሊወስድ ይችላል።

በሌላ በኩል ፥ ሴኔቱ ለዩክሬን ፣ ለእስራኤል እና ለሌሎች የባህር ማዶ የአሜሪካ አጋሮች የ95 ቢሊዮን ዶላር (5,419,427,000,000 ብር) የእርዳታ ጥቅል አፅድቆታል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ ፡-(@tikvahethiopia)