“ ባለፈው ሳምንት ብቻ 7 ሰዎች ናቸው የተገደሉት ” – ነዋሪዎች!!!!

በኮሬ ዞን ፤ #በታጣቂዎች አማካኝነት ንጹሃን ላይ የሚደርስ ጥቃት በእርቀ ሰላም ተፈቶ ቆሞ የነበረ ቢሆንም ከ4 ወራት ወዲህ በማገርሸቱ የንጹሐን ግድያ፣ የንብረት ዘረፋ እየተፈጸመ መሆኑን የዞኑ ባለስልጣትና ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

መንግሥት መፍትሄ እንዲሰጥም ተጠይቋል።

ባለስልጣናቱና ነዋሪዎቹ ለድርጊቱ  የ ” ኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ” ን ተጠያቂ አድርገዋል።

የዞኑ ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ተፈራ ቦንደሮ ምን አሉ ?

➡️ “ ከምዕራብ ጉጂ ዞን ጋላና ወረዳ የታጠቁ ኃይሎች በቀጠናው ላይ ገብተው 4 ሰዎችን በአንድ ቀን ገድለዋል። ”

➡️ “ የመንግሥት መዋቅር እዛ አካባቢ ላይ Functional ስላልሆነ ኦነግ ሸኔ በነጻነት ተንቀሳቅሰው በቀጠናው ላይ ጥቃት ይፈጽማሉ። ”

➡️ “ እርቅ ተፈጽሞ ከኀዳር 1 ቀን 2015 ዓ/ም ወዲህ ከጉጂ ዞን ጋ መልካም ግንኙነት ተፈጥሮ እንደነበር፣ ይሁን እንጂ ከ4 ወራት ወዲህ ታጣቂዎቹ እንደገና ጥቃት እያደረሱ ነው። ”

ቃላቸውን የሰጡን የቆቦ ቀበሌ ነዋሪ ምን አሉ ?

👉 “ ባለፈው ሳምንት ብቻ 7 ሰዎች ተገድለዋል። 4ቱ የቆቦ ቀበሌ ነዋሪዎች እሁድ ሚያዚያ 13 ቀን 2016 ዓ/ም ከብት በሚጠብቁበት ነው የተገደሉት። ”

👉 “ከዚያ በፊት ዳኖ ቀበሌ 2 ሰዎች ተገድለዋል። ሌላም የሞተ አለ። ”

👉 “ ታጣቂዎቹ #ከ2009 ዓ/ም ጀምሮ ጥቃት ያደርሱ ነበር በዚህም ከ100 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። ”

👉 “ በ2015 ዓ/ም እርቅ ተፈጽሞ ጥቃቱ ቆሞ ነበር። ከወራት ወዲህ ጥቃቱ አገርሽቶ በርካታ ሰዎች ተገድለዋል። ”

👉 “ በቆቦ ቀበሌ እርቁ ከተፈጸመ ወዲህ ብቻ 10 ሰዎች ተገድለዋል። ”

ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የኮሬ ዞን ኮሚዩኒኬሽን አካል ምን አሉ ?

▪️ “ በቀን 08/08/2016 የሁለት አርሶ አደሮች ሕይወትም አልፏል። እስከ ሚያዚያ 8/2016 ብቻ 19 ንጹሐን ከህዳር 1/2015 ዕርቅ በኋላ ተገድለዋል። ”

▪️ “ ከ19ኙ ሟቾች በተጨማሪ እሁድ ሚያዚያ 13 በቆቦ ቀበሌ፦

– ተመን እንግዳ ሶልዳንቶ

– ይርጋ ሚትኩ ሶልዳንቶ

– ነብዩ ቡና

– አባይ ፍቅሬ የተባሉ ሰዎች ተገድለዋል። ”

▪️ “ ንጹሐንን የገደሉ ለሕግ ይቅረቡ። ”

ጉዳዩን በተመለከተ ምላሽ ለማግኘት ወደ ኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ተደጋጋሚ ሙከራ ቢደረግም ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ለጊዜው ምላሻቸውን ማካተት አልተቻለም።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ ፡-(@tikvahethiopia)