በማሌዥያ ሁለት ወታደራዊ ሄሊኮፕተሮች በልምምድ እያሉ ተጋጭተው አስር ሰዎች ሞቱ

ሁለት የማሌዥያ አየር ኃይል ሄሊኮፕተሮች ለወታደራዊ ትዕይንት በልምምድ ላይ እያሉ መጋጨታቸውን ተከትሎ አስር ሰዎች ሞቱ።

በሄሊኮፕተሮቹ ውስጥ የነበሩት አስሩም ሰራተኞች ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿል።

አንደኛው ሄሊኮፕተር የሌላኛውን ሄሊኮፕተር የአናቱን ተሽከርካሪ ክፍል መምታቱን ተከትሎ በተፈጠረው ግጭትም ሁለቱም መሬት ላይ መውደቃቸውን የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ያወጣው ቪዲዮ አሳይቷል።

አደጋው የተፈጠረው የማሌዥያ የአየር ኃይል የጦር ሰፈር በሆነችው ሉሙት በተሰኘችው ከተማ በአገሬው ሰዓት አቆጣጠር ከጥዋቱ 3፡30 ገደማ ነው።

“በሄሊኮፕተሮቹ ውስጥ የነበሩ ሁሉም ሰዎች በስፍራው መሞታቸው ተረጋግጧል። አስከሬናቸውን ለመለየትም ወደ ወታደራዊ ሆስፒታል መላኩን” የማሌዥያ አየር ኃይል ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የአደጋውን መንስዔ የሚያጣራ ኮሚቴም እንደሚያቋቁም አክሏል።

ሰባት ሰዎችን ጭኖ የነበረው ኤችኦኤም ኤም503-3 የተሰኘው በመሮጫ ትራክ ላይ ተከስክሷል።

ሁለተኛው ሶስት ሰዎችን አሳፍሮ የነበረው ፌኔክ የተሰኘው ሄሊኮፕተር በአቅራቢው ባለ የመዋጫ ገንዳ ውስጥ ወድቋል። የአካባቢው እሳት እና ድንገተኛ ክፍል ስለ አደጋው ከጥዋቱ 3፡50 አካባቢ ሪፖርት ተደርጎልኛል ብሏል።

የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሒም “አገራችን ልብ በሚሰብር አሳዛኝ ክስተት በሐዘን ተውጣለች” በማለት በኤክስ ገጻቸው አስፍረዋል።

አክለውም በዚህ አደጋ ቤተሰቦቻቸውን፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ላጡ መጽናናትን ተመኝተው በዚህም ፈታኝ ወቅት ጥንካሬን እንዲሰጣቸው በጸሎት አስባቸዋለሁ ብለዋል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ ( ቢቢሲ ዜና )