የ3 ዓመት ሕፃናት በኢንተርኔት ለወሲባዊ ብዝበዛዎች እየተጋለጡ መሆኑን አንድ ድርጅት አስጠነቀቀ!!!!

ወሲባዊ ድርጊት አሳዳጆች ከስድስት ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት ስልካቸውን ተጠቅመው “አስፀያፊ” ድርጊት እንዲፈፅሙ እያደረጉ ነው ሲል የተራድዖ ድርጅት አስጠነቀቀ።

ኢንተርኔት ዋች ፋውንዴሽን የተሰኘው ተቋም በአውሮፓውያኑ 2023 ብቻ ከ2 ሺህ በላይ ሕፃናት በኢንተርኔት አማካይነት ወሲባዊ ብዝበዛ ደርሶባቸዋል ብሏል።

በቅርቡ ኦፍኮም የተባለው ድርጅት ያወጣው መረጃ መሠረት በጣም በርካታ ዕድሜያቸው ከ5-7 የሚሆን ሕፃናት የራሳቸው ዘመናዊ ተንቀሳቃሽ ስልክ አላቸው ይላል።

ይህን ማስጠንቀቂያ ተከትሎ የብሪታኒያው ደኅንነት ሚኒስትር ቶም ቱጌንዳት የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ብዝበዛን ለማስቆም መሥራት አለባቸው ብለዋል።

ሚኒስትሩ አክለው ቤተሰብ “ሕፃናት ማሕበራዊ ሚድያ እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው ሊነግሯቸው ይገባል፤ ምክንያቱም ሰላማዊ ነው ያላችሁት ማሕበራዊ ሚድያ አደጋ ሊኖረው ይችላል” የሚል መልዕክት አስተላለፈዋል።

አይደብሊውኤፍ የተሰኘው ተቋም ሕፃናት ላይ ወሲባዊ ብዝበዛ የሚያደርሱ ምስሎችን አስሶ በማስወገድ ላይ የተሰማራ ነው።

ተቋሙ በቅርቡ ባወጣው ዓመታዊ መግለጫው በ2023 ብቻ ኢንተርኔት ላይ 2401 ዕድሜያቸው ከሶስት እስከ ስድስት የሚሆን ሕፃናትን “ሰልፍ ጄኔሬትድ” ምስል ማግኘቱን ገልጧል።

 

“ሰልፍ ጄኔሬትድ” የሚባለው ምስል ወሲባዊ ቅሌተኞች ሕፃናትን በማሳመን አሊያም በማታለል ያልተገባ ድርጊት አንዲፈፅሙ የሚያደርጉበት ነው።

ከእነዚህ ምስሎች ከሰባቱ አንዱ እጅግ አሰቃቂ የሚባሉ ወሲባዊ ድርጊቶች በሕፃናት ሲተገበሩ የሚያሳዩ ሲሆን በተለይ ሕፃናት “ራቁታቸውን ቆመው” የሚታዩበት ይገኝበታል።

ተንታኞች እንደሚሉት እኒህ ምስሎች የሚወሰዱት ሕፃናቱ ክፍላቸው ውስጥ ብቻቸውን እያሉ አሊያም የወላጆቻቸው መፀዳጃ ክፍል ሆነው ወይመ ደግሞ ከሌሎች ሕፃናት [እህትና ወንድም፤ ጓደኛ] ጋር ሆነው ነው።

ብዙውን ጊዜ ሕፃናት ምስላቸው እየተቀዳ እንደሆነ የሚያውቁት ነገር የለም።

ተቋሙ ባወጣው ሪፖርት መሠረት የመሰል ምስሎች መጠን ከሌላው ጊዜ ሲነፃፀር የ22 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

የብሪታኒያ ባለሥልጣናት ሕፃናትን መጠበቅ የወላጅና አሳዳጊ ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችም የራሳቸውን አስተዋፅዖ ሊያደርጉ ይገባል ይላሉ።

ሕፃናት በኢንተርኔት አማካይነት የሚደርስባቸውን ወሲባዊ ብዝበዛ ለመግታት ሰው ሰራሽ ልኅቀት ጥቅም ላይ እንደሚያውል ኦንላይን ሴፍቲ አክት የተሰኘው ኮሚቲ ገልጧል።

ነገር ግን አይደብሊውኤፍ በጣም ፈጣን እርምጃ መወሰድ አለበት፤ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችም ቆመው ማየት አይገባቸውም ይላል።

አንዳንድ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ሰው ሰራሽ ልኅቀት በመጠቀም የሕፃናትን ብዝበዛን ጨምሮ ሌሎች የአጠቃቀም ሕግ የሚጥሱ ይዘቶችን ማጣራት ይዘዋል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ ፡-(BBC)