የ ” ቲክቶክ ” እገዳ በኪርጊስታን ተግባራዊ ሆነ።

ኪርጊስታን ” ቲክቶክ ” በመላ ሀገሪቱ  እንዲታገድ ውሳኔ ማስለፏ ይታወሳል በዚሁ ውሳኔ መሰረት የቴሌኮም አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች ትዕዛዙን ወደ መፈጸም #እርምጃ ገብተዋል።

በሀገሪቱ ” ቲክቶክ ” መስራት እንዳቆመም ተነግሯል።

ሰዎች መተግበሪያውን ሲከፍቱን የሚያገኙት መልዕክት ” Unable to load, please try again.” የሚል ነው።

ውሳኔው በሀገሪቱ ብሔራዊ ደህንነት መ/ቤት የተላለፈ ነው።

የኪርጊስታን ዲጂታል ሚኒስቴር ቲክቶክን የሚያስተዳድረው ‘ ባይት ዳንስ ‘ ኩባንያ ፥ ” #የልጆችን ፦

– አእምሯዊ፣

– አካላዊ፣

– መንፈሳዊ እና #ሥነምግባራዊ እድገትን ለመጠበቅ በህግ የተዘረዘሩ ህጋዊ መስፈርቶችን ማክበር አልቻለም ” ብሏል።

በዚህም ምክንያት ” ቲክቶክ ” በሀገሪቱ እንዳይሰራ ተደርጓል።

ውሳኔው የተቃወሙ አካላት ይህ ተገቢ እንዳልሆነ በመግለጽ ገደቡ እንዲነሳ ጠይቀዋል። ከገደብ ይልቅ ቁጥጥር ይደረግበት ብለዋል።

ከዚህ ቀደም የኪርጊስታን የባህል፣ ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ፥ ” ቲክቶክ ” የተሰኘው መተግበሪያ ለልጆች አእምሯዊ እድገት እና አጠቃላይ ደህንነት ጠንቅ እየሆነ ነው ” ማለቱ ይታወሳል።

መተግበሪያው #ህጻናት እጅግ ጎጂ ሊሆኑ የሚችሉ ይዘቶችን እንዳያገኙ ለመከላከል በቂ #መቆጣጠሪያ እንደሌለው ነበር የገለጸው።

በተጨማሪም ለተጠቃሚዎቹ ትክክለኛ የዕድሜ ማረጋገጫ እርምጃዎች እንደለለው እና ተጠቃሚዎችን በአጫጭር የቪዲዮ ክሊፖች ወደ ምናባዊ ግዛት በመሳብ #ሱስ የሚያስይዝ ይዘት እንዳለው አስረድቶ ነበር።

ሚኒስቴሩ ” ቲክቶክ ” በወጣቱ ትውልድ ደህንነት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳለው በአጠቃላይም ለትውልዱ ጠንቅ እየሆነ እንደመጣ አሳውቆ ነበር።

በሌላ በኩል ፤ አሜሪካ ውስጥ ከመረጃ ደህንነት ጋር በተያያዘ መተግበሪያው እንዲታገድ ከፍተኛ ግፊት እየተደረገ ሲሆን  ” ቲክቶክ ” ከቻይናው ኩባንያ ካልተፋታ / አሜሪካ የምትቆጣጠረው አይነት ካልሆነ በመላ ሀገሪቱ መታገድ ዕጣ ፋንታ ሊገጥመው ይችላል ተብሏል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ ፡-(@tikvahethiopia)