” የመምህራን የስነ-ልቦና ቁስል ሳይሽር ስለ የትምህርት ጥራት ማረጋገጥ ማሰብ ይከብዳል ”  – ማህበሩ….

የትግራይ መምህራን ማህበር በድጋሚ የመምህራን የ17 ወራት ውዙፍ ደመወዛቸው እንዲከፈል ጠየቀ።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደርንም ዳግም አስጠነቅቋል። 

ማህበሩ ሚያዚያ 8 በኣክሱም ከተማ 33ኛው ጉባኤውን አካሂዶ ነበር። በጉባኤው ማጠቃለያ ባወጣው የአቋም መግለጫ ” የትግራይ መምህራን የ17 ወራት ውዙፍ ደመወዛቸው እንዲከፈል ” ሲል ጠይቋል።  

የማህበሩ ስራ አስፈፃሚ እስከ ግንቦት 7 ቀን 2016 ዓ.ም ባለው ጊዜ ከሚመለከታቸው የጊዚያዊ አስተዳደሩ አመራሮች ጋር በመገናኘት ስለ ውዙፍ ደመወዝ መከፈል የመጨረሻ አቋሙ እንደሚያሳውቅ አመልክቷል።

ለጥያቄው በጊዜ ገድብ የተወሰነ አሳማኝ መልስ ካላገኘ ጠበቃ አቁሞ ክስ እንደሚመሰርት አሳውቋል።

” ተቃውሟችን እና ጥያቄያችን ትምህርት ቤቶች በመዝጋትና ተተኪ ዜጋ በመጉዳት የማሳካት ፍላጎት የለንም ” ያለው ማህበሩ ” ግዴታችን እየፈፀምን መብታችን እስከ ጫፍ እንጠይቃለን ” ብሏል።

” የመምህራን የስነ-ልቦና ቁስል ሳይሽር በትምህርት ስለሚገነባው ትውልድና የትምህርት ጥራት ማረጋገጥ ማሰብ ይከብዳል ”  ሲልም አክሏል።

ማህበሩ የመምህራን ጥያቄ እስኪመለስ ህጋዊ ተቋውሞ ማሰማቱን እንደሚቀጥል አረጋግጧል።

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ! https://t.me/ethioamazon

ምንጭ ፡-(@tikvahethiopia )