ቻይናዊ ሯጭን አሸናፊ ያደረጉት ኢትዮጵያዊ እና ኬንያዊ አትሌቶች እንዲሁም አሸናፊው ሜዳልያቸውን ተነጠቁ

በቤጂንግ የግማሽ ማራቶን የሩጫ ውድድር ቻይናዊ ሯጭን ሆን ብለው አሸናፊ አድርገውታል የተባሉት ኢትዮጵያዊ እና ኬንያዊ አትሌቶች እንዲሁም አሸናፊው ቻይናዊ ሜዳልያቸውን ተነጠቁ።

አንድ ኢትዮጵያዊ እና ሁለት ኬንያውያን አትሌቶች ሆን ብለው ቻይናዊ ሯጭ እንዲያሸንፍ ማድረጋቸው ምርመራ ከተካሄደበት በኋላም ነው ውሳኔው የተላለፈው።

ባለፈው ሳምንት እሁድ በነበረው ውድድር ቻይናዊው ሂ ጂ 1፡03፡44 በሆነ ሰዓት ሲያጠናቅቅ ኢትዮጵያዊው ደጀኔ ኃይሉ ሁለተኛ እንዲሁም ኬንያውያኑ አትሌቶች እኩል ሦስተኛ ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል ተብሏል።

ሶስቱ የምስራቅ አፍሪካ አትሌቶች ቻይናዊው ሯጭ ሆን ብለው እንዲያሸንፍ ማድረጋቸው ተዘግቦ ነበር።

ኢትዮጵያዊው ደጀኔ ሃይሉ፣ እና ሁለቱ ኬንያውያን አትሌቶች ሮበርት ኬተር እና ዊሊ ምናንጋት ፍጥነታቸውን በመቀነስ ቻይናዊው አትሌት እንዲያልፋቸው በጃቸው ምልክት የሚያሳዩበት ቪዲዮም ወጥቷል።

ሦስቱ አትሌቶች ከውድድሩ መጀመሪያ አንስቶ እስከ ማጠናቀቂያው ድረስ ቻይናዊውያን አትሌት አጅበው ሲሮጡ ነበር።

ኬንያዊው አትሌት ምናንጋት ሶስቱም አትሌቶች የሮጡት እንደ ውድድሩ አሯሯጭ (ፔስ ሜከር) መሆኑን ለቢቢሲ ተናግሮ ነበር።

ነገር ግን ምርመራውን የመራው የውድድሩ አዘጋጅ ኮሚቴ ከሶስቱ አትሌቶች መካከል አንዳቸውም በይፋ አሯሯጭ ( ፔስ ሜከር) ሆነው አለመመዝገባቸውን በመግለጽ ድርጊታቸው የውድድሩን ደንብ ይጥሳል ብሏል።

ኮሚቴው እንዳስታወቀው አትሌቶቹ ያሸነፏቸው “ሜዳሊያዎች፣ ዋንጫዎች እንዲሁም የገንዘብ ሽልማት” ይመለሳል ብሏል።

የቻይና መንግሥት ሚዲያ ሲሲቲቪ በበሉሉ አራቱም አትሌቶች መቀጣታቸውን እና ውጤታቸውም መሰረዙን ዘግቧል።

ከውድድሩ በኋላ የቻይና አትሌቲክስ ማህበሩ የአገሪቱን የሩጫ ውድድር አዘገጃጀት ለማሻሻል ጥረት አደርጋለሁ ብሏል።

ቻይናዊው ሯጭ ባለፈው ዓመት ሃንግዙ ግዛት በተካሄደው የእስያ ጨዋታዎች ላይ በማራቶን ውድድር ያሸነፈ ሲሆን የማራቶን ክብረ ወሰን ባለቤት ነው።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ ( ቢቢሲ ዜና )