ባይትዳንስ ‘ #ቲክቶክ ‘ ን #ለአሜሪካ ከመሸጥ አሜሪካ ውስጥ #ቢዘጋው እንደሚመርጥ ሮይተርስ ለኩባንያው ቅርብ የሆኑ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ዘገበ።

ኩባንያው በ’ ቲክቶክ ‘ ጉዳይ እስከመጨረሻው ያሉትን የህግ አማራጮችን ተጠቅሞ እንዳይታገድ ማድረግ ካልቻለ ፤ ለአሜሪካ ከመሸጥ ይልቅ እስከመጨረሻው #መዝጋት ይመርጣል ተብሏል።

አሁን ‘ ቲክቶክ ‘ የሚሰራበት #አልጎሪዝም ለኩባንያው እንደ ዋናው ነገር እንደሚቆጠርና በዚህ አልጎሪዝም መተገበሪያውን የመሸጥ እድሉ እጅግ ሲበዛ አነስተኛ እንደሆነ የኩባንያው ምንጮች ገልጸዋል።

በዚህም ፤ ለአሜሪካ ገዢ ከመሸጥ አሜሪካ ውስጥ እስከወዲያኛው ድረስ መዝጋትን እንደሚመርጥ ተጠቁሟል።

አሜሪካ ‘ ቲክቶክ ‘ እንዲሸጥ ከ9 ወር እስከ 1 ዓመት ገደብ አስቀምጣለች ካልሆነ ግን እስከ ወዲያኛው እንዲታገድ ሕግ አጽድቃለች።

በርካታ ጉዳዩን የሚከታተሉ የዘርፉ ሰዎች አሁን ባለው የአሜሪካ አቋም 170 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ያሉት ‘ ቲክቶክ ‘ እስከ ወዲያኛው ድረስ የመወገዱ ነገር እውን መሆኑ አይቀርም ብለዋል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ ( @tikvahethiopia )