” ልጄን አድኑልኝ ” – መምህርቷ እናት….

መምህርት አልሻምጌጥ ንጉስ ፤ ልጇ የአብቃል በተወለደ በሀያ አንድ ቀኑ ነው የልብ ህመም እንዳለበት ያወቀችው።

ላለፉት 5 አመታት የህጻናት የልብ ቀዶ ጥገና መዕከል አስመዝባ ብጠብቅም ወረፋ ሊደርሳት አልቻለም።

” አሁን ልጄ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ደረሰ ” ስትል ገልጻለች።

ከሀያ አንድ ቀኑ ጀምሮ ከሀዋሳ አዲስ አበባ እየተመላለሰች ሰርጀሪውን ስትጠብቅና ማስታገሻ መድሀኒት ስትጠቀም ብትቆይም እንደልጅነቱ መቦረቅ ያልቻለው የአብቃል  ” አሁን ላይ የልቡ ክፍተት አራት ሚሊ በመድረሱ እብጠት ፈጥሮበታል ” ስትል አስረድታችለ።

ይህ እብጠት ምግብ እንዳይረጋለት ከማድረጉ በላይ በአፍና በአፍንጫዉ ደም መውጣት መጀመሩ እና ድንገት በየሰአቱ እራሱን ከመሳቱ በተጨማሪ ፍጹም የድካም ስሜት ውስጥ እንዲገባ በማድረጉ ለቤተሰቡ ታላቅ ድንጋጤ ፈጥሯል።

ይህን ተከትሎ ጤና ባለሙያዎች በቶሎ ሰርጀሪዉ መሰራት እንዳለበት ቢናገሩም የመምህር ደሞዙን ከእለት ጉርስ አበቃቅቶ ለመድሀኒት ሲጠቀም ለቆዉ የመምህር አልሻምጌጥ ቤተሰብ ዱብ እዳ ሆኖበታል።

ቤተሰብም አሁን ላይ የሚያደርገዉ ጠፍቶበታል።

በጉዳዩ ላይ ለኢትዮጵያ ህዝብ በቲኪቫህ ኢትዮጵያ በኩል መልእክት አስተላልፉልኝ የምትለው እናት አሁን ላይ በግል ሆስፒታል ለሰርጀሪዉ ብቻ 650 ሽህ ብር እንደተጠየቀ በአጠቃላይ ከ800 እስከ 900  ሽህ ብር እንደሚያስፈልግ ገልጸለች።

ይህን ማድረግ ባለመቻሏ እና ገንዘብም ስለሌላት ልጇን አይኗ እያዬ ልታጣዉ መሆኑን በእንባ ተናግራለች።

በመሆኑም ፥ ” ደጉ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚቻለዉን አድርጎ ልጄን ያድንልኝ ” በማለት ተማጸናለች።

መምህር አልሻምጌጥ ንጉስን በስልክ ማነጋገር የሚፈልግ የግል ስልክ ቁጥሯ 0916155490 ነው። ይህ ደግሞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000243926053 የሂሳብ ቁጥሯ ነው።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ ፡-(@tikvahethiopia)