የቢትኮይን ፈጣሪ የሚባለው ሳቶሺ ናካሞቶን የት ነው ያለው?

ቢትኮይን የሁለት ትሪሊየን ዶላር የክሪፕቶከረንሲ ኢንደስትሪ ነው። በዓለም ዙሪያ በሚሊዮኖች ዘንድ ጥቅም ላይ ይውላል። በአንዲት ሀገር ኦፊሴላዊ መገበያያ ለመሆን በቅቷል።

ምንም እንኳ ቢትኮይን እንዲህ ቢስፋፋም አሁንም አንድ ሚስጥር ፍቺው አልተገኘም። የቢትኮይን ፈጣሪ የሚባለው ሳቶሺ ናካሞቶ ማን ነው?

ብዙዎች ይህን ጥያቄ ለመመለስ ሙከራ አድርገዋል። ብዙዎች አልተሳካላቸውም። በጥቅምት ወር የወጣ አንድ የኤችቢኦ ዘጋቢ ፊልም የቢትኮይን ፈጣሪ ካናዳዊው ፒተር ቶድ ነው ብሏል።

ፒተር ቶድ ተጠየቀ። የቢትኮይን ፈጣሪ አንተ ነህ ወይ? ነገር ግን ግለሰቡ የመለሰው መልስ ብዙዎችን ግራ ያጋባ ነው። “እኔ አይደለሁም” ነው ያለው።

ባለፈው ሐሙስ የቢትኮይን ፈጣሪ የሆነው ግለሰብ በቅርቡ በጋዜጣዊ መግለጫ ራሱን ይፋ እንደሚያደርግ ተነገረ።

ሳቶሺ ናካሞቶ ማነው የሚለው ጉዳይ እንዲህ አሳሳቢ የሆነው ዓለማችንን ከቀየሩ ሰዎች አንዱ ሆኖ እንዴት ማንነቱ አይታወቅም የሚለው ምላሽ አለማግኘቱ ነው።

አልፎም ከአንድ ሚሊዮን በላይ ቢትኮይን ባለቤት የሆነው ሳቶሺ ቢትኮይኑ ወደ ገንዘብ ቢመነዘር በርካታ ቢሊዮን ዶላሮች አሉት ማለት ነው።

የቢትኮይን ዋጋ ከምን ጊዜውም በላይ ጨምሯል።

ጋዜጣዊ መግለጫውን ያዘጋጁት ሰዎች ለመግቢያ መክፈያ ያስከፍላሉ። ከፊት ለፊት ለመቀመጥ 100 ፓውንድ ያስከፍላል። ጋዜጠኞች የፈለጉትን ለመጠየቅ ከፈለጉ ተጨማሪ 50 ፓውንድ ይከፍላሉ።

አዘጋጁ ቻርልስ አንደርሰን እንደሚለው ሳቶሺን በግል ቃለ-መጠይቅ ለማድረግ 500 ፓውንድ መክፈል ግድ ይላቸዋል።

የቢቢሲው ጆይ ታይዲ ገንዘቡን መክፈል አልችልም የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

እንደተጠበቀው መቀመጫዎች ይህን ያህል አልሞሉም።

አንድ ደርዘን የሚሆኑ ጋዜጠኞች መግለጫውን ለመታደም ተገኙ። ትንሽ ቆይቶ ግን አብዛኛው ጋዜጠኛ ሁኔታው ግር ይለው ጀመር።

የጋዜጣዊ መግለጫ አዘጋጆችም ሆኑ ሳቶሺ ነኝ የሚለው ግለሰብ የክስ ሒደት ላይ መሆናቸው የታወቀው ትንሽ ቆይቶ ነው። ሳቶሺ ነኝ ብለው በመቅረባቸው ነው ክስ ውስጥ የገቡት።

አንደርሰን ትንሽ ቆይቶ “ሳቶሺ” የተባለውን ሰው ወደ መድረክ ጠራው።

ስቴፈን ሞላሕ የተባለ ሰው ወደ መድረኩ መጥቶ “አዎ እዚህ የመጣሁት አንድ ነገር ግልፅ ለማድረግ ነው። እኔ ሳቶሺ ናካሞቶ ነኝ። በብሎክቼይን ቴክኖሎጂ ቢትኮይንን የፈጠርኩት እኔ ነኝ።”

ቀጥሎ ከጋዜጠኞች በርካታ ጥያቄዎች ይቀርቡለት ጀመር። ነገር ግን ግለሰቡ ለሚቀርቡለት ጥያቄዎች ትክክለኛውን ምላሽ እና ማብራሪያ ማቅረብ አልቻለም።

የቢቢሲው ጆይ እና ሌሎች ጋዜጠኞች የመግለጫውን አድራሻ ጥለው መውጣት ጀመሩ።

ሞላሕ ብቻ አይደለም “እኔ ሳቶሺ ናካሞቶ ነኝ” ብሎ ወደፊት ብቅ ብሎ የሚያውቀው። በርካቶች የቢትኮይን ፈጣሪ ነኝ ብለው ሳይሳካላቸው ቀርቷል።

በአውሮፓውያኑ 2014 የወጣ የኒውስዊክ ጋዜጣ ዘገባ ዶሪያን ናካሞቶ የተባለው ጃፓናዊ አሜሪካዊ ሰው ነው ቢትኮይንን የፈጠረው የሚል ዘገባ አስነብቧል።

ነገር ግን ግለሰቡ ራሱ እኔ አይደለሁም የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

ከአንድ ዓምተ በኋላ ደግሞ አውስትራሊያዊው የኮምፒውተር ሳይንቲስት ክሬግ ራይት የቢትኮይን ፈጣሪ ነው የሚል ወሬ ቢሰማም ክሬግ እኔ አይደለሁም ሲል አስተባብሏል።

ቢሊየነሩ እና የክሪፕቶ አቀንቃኙ ኢላን መስክም ይህ ስም ተሰጥቶት እኔ አይደለሁም የሚል ማስተባበያ ሰጥቷል።

ሳቶሺ ናካሞቶን ፍለጋው ቀጥሏል። ምናልባት አንድ ቀን ጥያቄው ምላሽ ያገኝ ይሆናል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብ/ኙ። https://ethio-amazon.com/

 

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

 

ምንጭ፡– (ቢቢሲ)