” ጥናቱ ሙሉ በሙሉ ቆሟል ” – የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ….

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር የሚገኙ የመንግሥት ተቋማት አገልግሎት የሚሰጡበትን ሰዓት ከስምንት ወደ 16 ሰዓት ለማራዘም የተጀመረው ጥናት መቆሙን የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታውቋል።

ጥናቱ የተጀመረው በከተማ አስተዳደሩ ሥር በሚገኙ የመንግሥት ተቋማት የሚሠሩ ሠራተኞች የግል ገቢ እንዲኖራቸው፣ እንዲሁም የከተማዋን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለማነቃቃት ታስቦ መሆኑን ቢሮው ማስታወቁ ይታወሳል።

አሁን ላይ ግን የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የሥራ ሰዓት ለማራዘም የተጀመረው ጥናት ሙሉ ለሙሉ ቆሟል፡፡

የከተማው የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ጣሰው ገብሬ (ዶ/ር) ፥ ” የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን የሥራ ሰዓት ለማራዘም መነሻ ጥናት ተደርጎ ነበር ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ የለም ” ሲሉ ለሪፖርተር ጋዜጣ ተናግረዋል።

ኃላፊው በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ መስጠት እንደማይፈልጉ ተናግረዋል።

ወደፊት የታሰበው አሠራር ተግባራዊ ይደረጋል አይደረግም የሚለውን እንደማያውቁ ገልጸዋል።

ጥናቱ የተጀመረው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር የሚገኙ መሥሪያ ቤቶችን የሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 አስቀድሞ ለማስጀመርና ከ11፡30 በኋላ እስከ ምሽት ለማስቀጠል ታቅዶ ነበር፡፡

ዕቅዱ ይፋ የተደረገው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የከተማዋ መ/ቤቶች አገልግሎት አሰጣጥን አስመልክቶ መሆኑን ቢሮው ግንቦት 3 ቀን 2015 ዓ.ም. ከባለድርሻ አካላት ጋር ባደረገው ውይይት መግለጹን ሪፖርተር ጋዜጣ በዘገባው አስታውሷል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ ፡-(@tikvahethiopia)