የደቡብ አፍሪካ ፓሊስ ‘ህገወጥ ቆፋሪዎችን’ ከማዕድን ማውጫ ለማስወጣት ምግብ እንዲቋረጥባቸው አደረገ

የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ህገወጥ ያላቸውን በመቶዎች የሚቆጠሩ ማዕድን ቆፋሪዎችን ምግብ እና ውሃ በማቋረጥ ከነበሩበት የማዕድን ማውጫ እንዲወጡ በማስገደድ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለጸ።

በቁጥጥር ስር የዋሉት 540 ግለሰቦች ሲሆኑ ከስራ ውጭ ከተደረገ የማዕድን ማውጫ እንደነበሩ ተገልጿል።

የጸጥታ ሃይሎች በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ማዕድን አውጪዎቹን ከጉድጓዱ ውስጥ ለማስወጣት ሲሉ ምግብ እና ውሃ እንዳይቀርብላቸው ከልክለዋል።

“ረሃብ እና የውሃ ጥም” ያጠቃቸው የማዕድን ቆፋሪዎች ከጉድጓዱ ለመውጣት መገደዳቸውን ፖሊስ ተናግሯል።

ከቅዳሜ ጀምሮ በሰሜን ኦርክኒ ከተማ ውስጥ ከሚገኘው የማዕድን ማውጫው ውስጥ አንድ በአንድ መውጣት ጀምረዋል። አሁንም ግን በመቶዎች የሚቆጠሩ በማዕድን ማውጫው ውስጥ እንዳሉ ይገመታል።

እሑድ ዕለት የሀገሪቱ የፖሊስ አዛዥ የጸጥታ ሃይሎች ከኃላፊነታቸው “ወደ ኋላ እንዳይሉ” እና “የህግ የበላይነት መከበሩን እንዲያረጋግጡ” ባወጡት መግለጫ ጠይቀዋል።

መግለጫው አክሎም በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የጸጥታ ኃይሎች “ከሥራ ውጭ በተደረጉት የማዕድን ማውጫዎች አካባቢ ያሉ ማህበረሰቦች ምግብ፣ ውሃ እና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮችን ለህገ-ወጥ ማዕድን አውጪዎች እንዳያደርሱ አግደዋል” ብሏል።

ቅዳሜ ዕለት 225 ማእድን አውጪዎች መውጣታቸወን ፖሊስ ገልጿል። አሁንም ግን “ሺህ እንኳን ባይሆኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ” ከመሬት በታች ናቸው ተብሎ ይታሰባል ሲል አክሎ ነበር።

ፖሊስ እሑድ ዕለት በሰጠው መረጃ ከማዕድን ማውጫው ውስጥ ተጨማሪ 340 ሰዎች መውጣታቸውን እና በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጿል።

“ዛማ ዛማስ” (በዙሉ ቋንቋ ዕድላቸውን የሚሞክሩ እንደማለት ነው) በመባል የሚታወቁት በሺዎች የሚቆጠሩ ህገ-ወጥ ማዕድን ማውጫዎች በአካባቢው ይንቀሳቀሳሉ።

የፖሊስ ኮሚሽነሩ ሌተናል ጀነራል ሻድራክ ሲቢያ እንደገለጹት ከሆነ ከታህሳስ 2023 ወዲህ በሰባት ግዛቶች ከ13 ሺህ 690 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

“283 ዶላር በጥሬ ገንዘብ እና ያልተቆረጡ እና 1.8 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ አልማዞች ይዘናል” ብለዋል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብ/ኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ፡– (ቢቢሲ)