የትራፊክ አደጋ የበርካቶች ህይወት እየቀጠፈ ይገኛል።

በዚህ ወር ብቻ ፦

– በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 2 ሰዎች ሲሞቱ 5 ሰዎች ተጎድተዋል።

– በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ወረዳ ከኔጌሌ ወደ ዶዶላ ተሳፋሪዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ‘አላንቱ’ ላይ ከ ” ሲኖትራክ ” የጭነት መኪና ጋር ተጋጭቶ የ15 ሰዎች ህይወት አልፏል። ሌሎችም ተጎድተዋል።

– በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በካፋ ዞን ጨና ወረዳ ፤ ከዋቻ ወደ ቦንጋ ሲጓዝ የነበረ ዶልፊን ተሸከርካሪ እና ከሚዛን ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ #ሲኖ_ትራክ ተሸከርካሪ በጨና ወረዳ ቦባ በላ ቀበሌ ተጋጭተው 5 ሰዎች ሲሞቱ 13 ሰዎች ተጎድተዋል።

–  በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን በእዣ ወረዳ ወርት በተባለች ቀበሌ እንጨት ጭኖ ሲጓዝ የነበረ #ሲኖ_ትራክ የጭነት ተሽከርካሪ በደረሰበት የመገልበጥ አደጋ   የ6 ወጣቶች ህይወት ወዲያዉ ሲያልፍ በ10 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሷል። አደጋዉን የከፋ ያደረገው ሲኖ ትራኩ  ወጣቶችን እንጨት ላይ አሳፍሮ እየተጓዘ ባለበት ወቅት አደጋው በመድረሱ ነው።

ከላይ በተጠቀሰው እና በይፋ በታወቀው ብቻ 28 ዜጎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን አጥተዋል። በርካቶች የአካል ጉዳተኛ ሆነው።

እባካችሁ ጥንቃቄ አይለያችሁ !

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ ፡-(@tikvahethiopia)