የታገቱ ሰዎች ጉዳይ ከምን ደረሰ ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ፦
➡️ ወደ ባቱ ሲጓዙ በታጣቂዎች ስለታገቱና እስካሁን ስላልተለቀቁ 3 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሠራተኞች ጉዳይ፤ (https://t.me/tikvahethiopia/86971?single)
➡️ ልጃቸው በሊቢያ ስለታገተባቸው የሀዋሳዋ እናት ፣ (https://t.me/tikvahethiopia/86852?single)
➡️ ልጃቸው በሊቢያ ስለታገተባቸው የአዲስ አበባው አባት ፤ (https://t.me/tikvahethiopia/86957?single)
➡️ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ስትጓዝ የመን ላይ ታግታ 300 ሺህ ብር ስለተጠየቀባት ወጣት (https://t.me/tikvahethiopia/87107?single) መረጃዎችን ማድረሱ ይታወሳል።
ስለታጋቾች አሁንስ #ምን_አዲስ_ነገር_አለ ? በሚል ቤተሰቦቻቸውን ጠይቋል።
የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ታጋቾችን በተመለከተ አዲስ ነገር የጠየቅናቸው የአንዱ ታጋች እህት ወይዘሮ ራሄል ሶስቱም #እንዳልተለቀቁ ገልጸው ፤ “ ምንም አይነት ፍንጭ የሚሰጠንም አጣን። የት እንሂድ ? ምን እናድርግ ? ” ሲሉ በሀዘን ጠይቀዋል።
ልጃቸው በሊቢያ እንደታገተባቸው ገልጸው የነበሩት የሀዋሳዋ ወይዘሮ ገነት ጥላሁን ፥ “ አሁንማ ‘ ፓሊስ ከቧቸዋል ’ ተብሎ ስልክም ብንደውል አይነሳም። ስልካቸው ከጠፋ ከ15 ቀናት በላይ ሆኗል ” ሲሉ ገልጸዋል።
“ ትሪፓሊ ከተማ ከደረሱት ውስጥ መረጃ ስንጠይቅ ‘ፓሊስ መጥቶባቸው ነው ፤ ከበዋቸዋል አካባቢውን’ ” እንዳሏቸው ገልጸዋል።
“ ደላላውን 1 ጊዜ ብቻ አግኝቸው ‘ ፓሊስ ስለመጣብን ሌላ መጋዘን ወስደናቸዋል ’ አለኝ ” ሲሉ ተናግረዋል።
በተመሳሳይ ልጃቸው በሊቢያ ታግቶባቸው 700 ሺሕ ከከፈሉ በኋላ በድጋሚ 400 ሺሕ ብር ተጠይቀው የነበሩት የታጋች አባት አቶ አማረ አለም ፣ ለ2ኛ ጊዜ የተጠየቁትን ገንዘብ ካርታ አስይዘው ተበድረው ከላኩ በኋላ ልጃቸው #እንደተለቀቀ ባሕሩን ለመሻገር አስቦ ሞገድ ስለተነሳ ገና እየጠበቀ እንደሆነ ገልጸዋል።
ሳዑዲ ለመሄድ ” ራጎ ” ላይ ስትደርስ በደላሎች 300 ሺሕ ብር የተጠየቀባት ታጋች ቤተሰቦች በበኩላቸው፣ ገንዘቡ ስላልተሟላ ገና እንዳልተላከ፣ ደላሎቹን ጊዜ እንዲሰጧቸው እየጠየቁ መሆናቸውን አስረድተዋል።
ውድ ቤተሰቦቻችን ፤ እገዛችሁን ጠይቀው የነበሩት ሁሉም የታጋቾች ቤተሰቦች ለረዷቸው ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።
በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ ብቻ ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤ ለተጨማሪ መረጃ ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/
ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon
ምንጭ (@tikvahethiopia )