የማንቸስተር ሲቲው ሮድሪ የባለን ዶር አሸናፊ ሆነ
የማንቸስተር ሲቲው ስፔናዊ አማካይ ሮድሪ የባለን ደኦር አሸናፊ ሆነ።
ባለፈው የውድድር ዓመት ከተሰለፈባቸው ጨዋታዎች በአንዱ ብቻ የተሸነፈው አማካዩ አገሩን የ2024 አውሮፓ ዋንጫ አሸናፊ አድርጓል።
ከሲቲ ጋር ደግሞ የፕሪሚር ሊጉን፣ የአውሮፓ ሱፐር ሊግ እና የዓለም የክለቦች ዋንጫን ማሳካት ችሏል።
በሲቲ ታሪክ የመጀመሪያው የባለን ዶር አሸናፊ ለመሆን የበቃው ሮድሪ የሪያል ማድሪዱን ቪንሺየስ ጁኒየርን በመቅደም ሽልማቱን በእጁ አስገብቷል።
እንግሊዛዊው ጁድ ቤሊንግሃም በሦስተኛነት አጠናቋል።
ሪያል ማድሪድ የዓመቱ ምርጥ ቡድን ሲባል አሰልጣኙ ካርሎ አንቸሎቲ ደግሞ የዓመቱ ኮከብ አሰልጣኝ ተብለዋል። የስፔኑ ክለብ ተወካዮች በሥነ ሥርዓቱ ላይ ቀርበው ሽልማታቸውን ሳይቀበሉ ቀርተዋል።
ማድሪዶች ራሳቸውን ያገለሉት ቪንሺየስ ጁኒር የባለን ዶር አሸናፊ አለመሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ ነው ተብሏል።
“ለእኔም፣ ለቤተሰቦቼም ሆነ ለአገሬ ልዩ ቀን ነው” ሲል ሮድሪ ሽልማቱን በተቀበለበት ወቅት ተናግሯል።
“ዛሬ ድሉ ለእኔ ሳይሆን ለስፔን እግር ኳስ ነው። እንደ አንድሬስ ኢኔሽታ፣ ዣቪ ሄርናንዴዝ፣ ኢከር ካስያስ፣ ሰርጂዮ ቡስኬት ያሉና እና ማሸነፍ ይገባቸው የነበሩ ተጫዋቾች ድል ነው” ብሏል።
ባለን ዶር በፊፋ የአገራት ደረጃ እስከመቶ ባለው ዝርዝር ውስጥ በሚገኙ አገራት የሚሠሩ ጋዜጠኞች በሚሰጡት ድምጽ የሚሰጥ ሽልማት ነው።
ከ2003 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊዮኔል ሜሲ (8 ጊዜ ተሸላሚ) እና ክርስቲያኖ ሮናልዶ (5 ጊዜ) የሽልማት ስነ ስርዓቱ ላይ ዕጩ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
ሮድሪ ባለፈው የውድድር ዓመት በሽልማቱ አምስተኛ ደረጃ ለመቀመጥ ችሎ ነበር።
የከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎች ሽልማት የሆነውን የገርድ ሙለር ዋንጫ ደግሞ እኩል 52 ጎሎችን ያስቆጠሩት ሃሪ ኬን እና ኪሊያን ምባፔ ተጋርተውታል።
የወጣቶች ኮከብ ተጫዋች ሽልማት የሆነውን ኮፓ ዋንጫ ስፔናዊው የባርሴሎና የክንፍ መስመር ተጫዋች ላሚን ያማል አሸንፏል።
የ17 ዓመቱ ያማል ለባርሴሎና 50 ጨዋታዎችን ተሰልፎ ሰባት ጎሎችን ሲያስቆጥር ሰባት ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አቀብሏል።
ለምርጥ ኮከብ ግብ ጠባቂ የሚሰጠውን የያሺን ዋንጫን ደግሞ አርጀንቲናዊው የአስቶን ቪላ የግብ ዘብ ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ ለተከታታይ ሁለተኛ ጊዜ ለማሸነፍ ችሏል።
የባልንዶር ምርጥ 10 ተጫዋቾች
- ሮድሪ (ስፔን እና ማንቸስተር ሲቲ)
- ቪንሺየስ ጁኒየር (ብራዚል እና ሪያል ማድሪድ)
- ጁድ ቤሊንግሃም (እንግሊዝ እና ሪያል ማድሪድ)
- ዳኒ ካርቫሀል (ስፔን እና ሪያል ማድሪድ)
- ኧርሊንግ ሃላንድ (ኖርዌይ እና ማንቸስተር ሲቲ)
- ኪሊያን ምባፔ (ፈረንሳይ እና ሪያል ማድሪድ)
- ላውታሮ ማርቲኔዝ (አርጀንቲና እና ኢንተር ሚላን)
- ላሚን ያማል (ስፔን እና ባርሴሎና)
- ቶኒ ክሩስ (ጀርመን እና ሪያል ማድሪድ)
- ሃሪ ኬን (እንግሊዝ እና ባየር ሙኒክ)
በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ ብቻ ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤ ለተጨማሪ መረጃ ድህረ ገጻችንን ይጎብ/ኙ። https://ethio-amazon.com/
ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon
ምንጭ፡– (ቢቢሲ)