” ቲክቶክ ላይት ” ጥያቄ ቀረበበት።

አዲሱ መተግበሪያው ‘ ቲክቶክ ላይት ‘ በፈረንሳይ እና ስፔይን አገልግሎት የጀመረው ቲክቶክ በህጻናት እና ተጠቃሚዎች የአዕምሮ ጤንነት ላይ ሊያስከትል ስለሚችለው አደጋ ያለውን ግምገማ በ24 ሰዓት ውስጥ እንዲያቀርብ ዛሬ የአውሮፓ ኮሚሽን ጠየቀ።

ከዋናው ቲክቶክ መተግበሪያ አነስ ብሎ የወጣው የቲክቶክ መተገበሪያ ተጠቃሚዎች #ተከፍሏቸው የቪዲዮ ምስሎችን እንዲመለከቱ በማድረግ በሚያስቆጥሯቸው ነጥቦች የመግዛት አቅምና ዋጋ ያላቸውን የስጦታ ካርዶችን የሚሽልም ነው፡፡

በመተግበሪያው ተሳታፊ ለመሆን ተጠቃሚዎች ቢያንስ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

ሽልማቱን ለማግኘት በቀን እስከ 1.06 ዶላር የሚደርስ ሽልማት ለማግኘት በየቀኑ አንድ ሰዐት ድረስ ቪዲዮውን መመልከት ይችላሉ፡፡

የአውሮፓ ኮሚሽን የቻይናው ቲክቶክ ባለቤት ባይትዳንስ (ByteDance) መተግበሪያውን ከመልቀቁ በፊት ሊያስከትል ስለሚችለው አደጋ ቁጥጥርና ጥንቃቄ ግምገማ ማድረግ ነበረበት ብሏል።

ጥያቄው የቀረበው ቲክቶክ ያወጣው አዲሱ ” Task and Reward Lite ” የተባለው መተግበሪያ፣ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ሕፃናትን ደህንነት እንዲሁም በተጠቃሚዎች የአእምሮ ጤና ላይ ፣ በተለይ ሱስ አስያዥ ባህሪን ከማነሳሳት ጋር ተያይዞ ሊያመጣ የሚችለውን ተፅእኖ መሰረት በማድረግ ነው ” ሲል የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

መተግበሪያው ሊያስከትለው ስለሚችለው አደጋ ቁጥጥር እንዲሁም ጥንቃቄ ያለውን ግምገማ እንዲያቀርብ ከተሰጠው የ24-ሰዐት የጊዜ ገደብ ባሻገር፣ ቲክቶክ የተጠየቀውን ተጨማሪ መረጃ እ ኤ አ እስከ ሚያዝያ 26 ድረስ መስጠት አለበት ሲል ኮሚሽኑ አሳስቧል።

የቲክቶክ ቃል አቀባይ ፥ ” አዲሱን መተግበሪያ በተመለከተ ከኮሚሽኑ ጋር በቀጥታ ተገናኝተናል፣ ለቀረበልን ጥያቄም ተገቢ ምላሽ እንሰጣለን ” ማለታቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ ፡-(@tikvahethiopia)