በአየርላንድ አንድ ግለሰብ አጥር ላይ በሚስማሮች የመቸንከር ጥቃት ተፈጸመበት

በሰሜናዊ አየርላንድ ቡሽሚልስ ግዛት በአንድ የመኪና ማቆሚያ ስፍራ አንድ ግለሰብ በአጥር ላይ ሁለት እጆቹ በሚስማሮች ተቸንክረው ተገኙ።

ጭካኔ የተሞላበት ጥቃት የተፈጸመበት በ20ዎቹ የዕድሜ ክልል የሚገኘው ይህ ግለሰብ ወደ ሆስፒታል መወሰዱም ተነግሯል።

ጥቃቱ የተፈጸመው ቅዳሜ ከእኩለ ሌሊት በኋላ መሆኑ ተገልጿል።

በዱንዳራቭ ፓርክ አቅራቢያ በሚገኘው የመኪና ማቆሚያ ስፍራ ጥቃት የተፈጸመበት ግለሰብ ንብረት የሆነ አንድ መኪና እና ሌላ ተጨማሪ ተቃጥለው ተገኝተዋል።

ፖሊስ የአየርላንድ ታጣቂ ቡድን ተሳትፎ ሊኖረው እንደሚችል በመጠርጠር ምርመራ መክፈቱን አስታውቋል።

በአቅራቢያው ባሉ የህዝብ መጸዳጃ ቤቶች ላይ የተሳሉ ስዕሎች እና የሰፈሩ መልዕክቶች ከጥቃቱ እና ከመኪናዎቹ ቃጠሎዎች ጋር እንደሚያያዝ ተነግሯል።

የሰሜን አየርላንድ ፖሊስ አገልግሎት ግለሰቡ በህይወቱ ላይ ጠባሳ ሊያስቀር የሚችል ጥቃት እንደደረሰበት ገልጾ ለህይወቱ አስጊ የሆኑ ጉዳቶች እንዳልደረሱበት ተናግሯል።

በተጨማሪም የደረሰበት “ክፋት የተሞላበት ጥቃት” እንደሆነም ፖሊስ በዚህ መግለጫው አክሏል።

“የምንኖርበት ዴሞክራሲያዊ ማህበረሰብ ለዚህ ጥቃት ምንም አይነት ማመኻኛ የለውም። ጥቃት አድራሾች ማህበረሰባቸውን ጭካኔ በተሞላባቸው ጥቃቶች እና በማስፈራራት ለመቆጣጠር እየሞከሩ ነው” ብሏል ፖሊስ

የሰሜን አየርላንድ የእሳት አደጋ እና የነፍስ አድን አገልግሎት ሰራተኞች በቦታው ተገኝተው በሁለቱም ተሽከርካሪዎች ላይ በቃጠሎ የደረሰውን የከፋ ጉዳት ገምግመዋል።

የፖሊስ አገልግሎት ረዳት ዋና ኮንስታብል ቦቢ ሲንግልተን ጥቃቱን “በጣም አስደንጋጭ እና ጭካኔ እና ክፋት የተሞላበት” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

“እንዲህ አይነት የከፉ ክስተቶች ያለፈ ታሪካችን አካል ናቸው ብለን እናስብ ነበር” ብለዋል።

ምንም እንኳን ስለ ጥቃቱ ሙሉ ለሙሉ ለመናገር ጊዜው ገና ቢሆንም ከአየርላንድ ታጣቂ ቡድን ጥቃት ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው ገልጸው አንደኛው ምርመራው ወደዚያ እንደሚያተኩር ገልጸዋል።

አክለውም ጥቃቱ የተፈጸመው በመኖሪያ ቤቶች አካባቢ ቢሆንም ከሌላ አገር የሚመጡ ቱሪስቶች የሚያርፉባቸው ሆቴሎች መገኛ መሆኑንም ተናግረዋል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ ( ቢቢሲ ዜና )