በሰሀራ በረሀ ለ50 ዓመታት ያልታየ ዶፍ ዝናብ መውረዱን የሳተላይት ምስሎች አሳዩ

ደቡብ ምስራቅ ሞሮኮ በሚገኘው የሰሀራ በረሀ ላይ በ50 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ዶፍ ዝናብ መጣሉን የሳተላይት ምስሎች አስመለከቱ።

ለሁለት ቀናት ተከታትሎ የዘነበው ከባድ ዝናብን ተከትሎ ነው በበረሀው ውሀ መከማቸት የጀመረው።

የሰሜን፣ ማዕከላዊ እና ምዕራብ አፍሪካ ሀገራትን አካልሎ የተዘረጋው የሰሀራ በረሀ በዓለማችን ረዥሙ እና ሞቃታማው በረሀ ነው።

“በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲህ ያለ ዝናብ ከጣለ ቆይቷል። ምናልባትም ከ30 እና 50 ዓመታት በፊት ነው” ሲሉ የሞሮኮ ሜቴዮሮሎጂ ኤጀንሲ ኃላፊ ሆሲን ዩዋቤብ ለአሶሺየትድ ፕረስ ይናገራሉ።ደቡብ ምስራቅ ሞሮኮ

ደቡብ ምስራቅ ሞሮኮ በዓለማችን እጅግ ሞቃታማ ደረቅ ከሚባሉ ሥፍራዎች አንዱ ሲሆን ዝናብ የሚያጋጥመው በዓመታት አንድ ጊዜ ቢሆን ነው።

ከሞሮኮ ዋና ከተማ ራባት 450 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ታፎናይት በ24 ሰዓታት ውስጥ 100 ሚሊሌትር አሊያም 3.9 ኢንች የሚረዝም ዝናብ ተመዝግቧል።

የአየር ትንበያ ሙያተኞች መሰል ዝናብን ‘ኤክስትራትሮፒካል ስቶርም’ ሲሉ ይጠሩታል። “አየሩ በርካታ እርጥበት ሲይዝ፤ ወደላይ መትነን ይጀምራል፤ ይህ ደግሞ ዝናብ ሊያስከትል ይችላል” ሲል የሞሮኮ አየር ትንበያ ኤጀንሲ ለኤፒ ተናግሯል።ደቡብ ምስራቅ ሞሮኮ

የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ተቋም ናሳ ይፋ ያደረጋቸው ምስሎች እንደሚያሳዩት በኃይለኛው ዝናብ ምክንያት በዛጎራ እና ታታ ከተማዎች መካከል ያለው ሐይቅ ሞልቷል። ይህ ሐይቅ ላለፉት 50 ዓመታት ደርቆ ነበር የቆየው።

የዓለም አየር ትንበያ ድርጅት እንደሚለው በዓለም ዙሪያ የዝናብ ጉዳይ እጅግ ተለዋዋጭ እየሆነ መጥቷል።የሞሮኮዋ ሜርዙጋ በረሃ ከዝናቡ በፊት ይህን ትመስል ነበር

“የሙቀት መጠን እየጨመረ ሲመጣ ሀይድሮሎጂካል ሳይክል የሚባለው ዑደት እየተፋጠነ ነው” ይላሉ የዓለም አየር ትንበያ ድርጅት ዋና ፀሐፊ ሴሌስት ሳውሎ።

ፀሐፊዋ በሰጡት መግለጫ የዝናብ ነገር “በጣም ተለዋዋጭ እና መገመት የሚከብድ እየሆነ መጥቷል” ብለው “አሁን እየገጠመን ያለው ችግር ወይ ብዙ ዝናብ አሊያም በጣም ትንሽ እየሆነ መምጣቱ ነው” ሲሉ ያስረዳሉ።

የዓለም ሙቀት መጠን እየጨመረ በመምጣቱ አስከፊ የሚባሉ የአየር ፀባይ ለውጦች እየታዩ ነው። ሳይንቲስቶች በሚመጡት ዓመታት ተመሳሳይ ክስተት ሰሀራ በረሀ ላይ ልናይ እንችላለን ይላሉ።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብ/ኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ፡– (ቢቢሲ)