Home The Observer’s Eye (የታዛቢ አይኖች)

The Observer’s Eye (የታዛቢ አይኖች)

ወደዳችሁም ጠላችሁም እኛ ኢትዮጵያውያን ነን:: ሌላ ምድር.. ሌላ ኣገር የለንም:: ወላይታነት ኢትዮጵያዊነት ነው… በኦሮሞነት ውስጥ ኢትዮጵያዊነት ኣለ…  ትግራዋይነት ኢትዪጵያዊነት ነው.. ባማራነት ውስጥ   ኢትዮጵያዊነት ኣለ :: ኣገውና ሽናሻ ቅማንትነትና ፈላሻ ጉራጌነትና ሃመር ኣጋሜነትና ሽዋ በር የኢትዮጵያውነት ውበት.. የኢትዮጵያዊነት ፈርጦች ናቸው ::
እነዚህ ሁሉ የኢትዮጵያ ዘምባቦች ናቸው:: በባህር ዳር የተተተከለች ዘምባባ ንፋስ እንደሚያወዛውዛት ሁሉ ንፋስ ሲመጣ እነዚህ ሁሉ ኣብረው ይወዛወዛሉ.. ከንፋሱ ጋር ያዘማሉ.. ንፋሱ ሲያልፍ ደሞ ኣብረው ቀና ይላሉ:: ወደዳችሁም ጠላችሁም እኛ ሁላችን ኢትዮጵያውያን ነን:: ሌላ ኣገር ሌላ ምድር የለንም:: ኣበባ ኣንድ ኣይነት ቀለም ቢኖረው ኖሮ ኣያምርም ነበር የኣበባ ውበት ነጭ ሮዝ ወይን ጠጅ ቀይ ቢጫ ውሃ ሰማያዊ በመሆኑ ኣበባን ኣይቶ የሚያልፍ የለም:: ስራ ቡዙ የሚባሉት ንቦች እንኴን ለማረፊያነት የሚመርጡት ኣበቦችን ነው:: እንደ ኣበቦች ለማማር እንደ ኣበቦች ማረፊያ እንድንሆን እጅ -ለእጅ መያያዝ ኣለብን:: ኢትዮጵያዊነት በዚህ ይገለጻል:: ኢትዮጵያዊነት በዚህ ይታያል::

 

እኔ የማውቃቸው የእምነት ኣባቶች የሚኖሩት በደሳሳ ጎጆ ጥሬ እየቆረጠሙ ወይም ትልቅ የዋርካ ዛፍን ጥላ ኣድርገው ቅዱሳትን መጽሃፍትን በማንበብና መንፈሳዊ ሜደቴት በማድረግ ካምላካቸው ጋር ሲገናኙ ነው:: የዛሬዎቹ ኣባቶቻችን በቪላ ወይም mansion የሚኖሩ ሲሆን ታቦት ሲወጣ የሚዘመረው ዝማሬ ሲዘመርላቸው ለኔ ኣይገባም!! የማይሉ ዝማሬውን በጸጋ የሚቀበሉ እንደውም ለክብራቸው እንደተዘመረ ኣድርገው የሚያስቡ ልበ ደንዳኖች ናቸው::

ቪዲዮውን ይመልከቱ…..

https://www.facebook.com/444956259029416/videos/464449787080063/

 

ይሄን ቪዲዮ  ( below  is the  link of the  video..)  ሳይ ሳቄ  መጣ….  ሰውየው  መምሬ  ግርማ  (ባንዳንዶች  ኣጠራር  መ ስ ህ በ ዛር ግርማ
)  ተፈተዋል :: lol…

መልካም!!   ለዘላለም እስር ቤት  እንዲኖሩ ወይም እንዲቆዩ ማንም ኣይፈልግም ሰው ከሰራው   እስር  ቤት  መውጣት  ቀላል ነገር ነው  እጊዚኣብሄር  ከሰራው የህሊናና  የመንፈስ  እስር  እንደ መውጣት  የሚከብድ ነገር የለም::  ኣባታችን ተፈቱ እያሉ  እልልታ ከማብዛት   ይልቅ  ለምን ታሰሩ ብሎ መጠየቅ ያባት ነው::  እኔ  እንደገባኝ  የተፈቱቱት  የዋስ  መብታቸው ተከብሮላቸው  እንጂ ከተከሰሰሱበት  የማጭበርበር  ወንጀል ( felony )  ነጻ ሆነው  ኣይደለም::  ኣቶ ደጀኔ የሚባል  ኢትዮጵያ በላቡና በወዙ  ያገኘውን  ሃብት ኣባታችን   “ብሩን ላባዛልህ”  ብለው ሿሿ   ኣድርገውታል..lol ::  ይሄ  ነው  ችግሩ  ሌላ ችግር የለም…. ኣይናችን  ብቻ ሳይሆን ልባችንም መመልከት ይጀምር እንጂ  ጎበዝ  ኢንዴት  ነው ነገሩ….

ዜናዎቻችን በተከታታይ እንዲደርሷችሁ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ “Like” ወይም “Comment” ወይም “Share” ያድርጉ!!
https://www.facebook.com/pages/Ethiopian-This-Week/114125298610656?pnref=story

 

 

እስኪ ሰሞኑን ያስገረመኝና ፈገግ ያደረገኝን ነገር ልቀቅባችሁ ..
ባገራችን ውስጥ ማስተር ፕላኑን ኣስመልክቶ በተፈጠረው ችግርና የቅማንትን ጉዳይ በተመለከተ በተፈጠረው ውዝግብ ኣሉ የሚባሉና በውጭ ኣገር ጭብጨባ የሚበዛላቸው የዲያስፖራ ዶክተሮች ወይንም ማስተሮች ወይንም ኣንዳንዶቹ የፓልቶክ የጦር ኣለቆች የሆኑ በተለያየ ሚዲያ ግጭቱን ኣስመልክቶ እነሱ እነደሚሉት ሳይንሳዊ ትንታኔ ( analysis and synthesis) ይሰጡ ነበር:: እኔ ዶክትሬታቸውን በምን እንደሰሩ ኣላውቅም እዚህ ኣገር ግን ጥሩ ጠገራ ብር የምት ሰራ ከሆንክ ና ለሚዲያ ሰዎች ቀረብ ብለህ ከተገኘህ ስለ ስንዴ ኣመጣጥ ኣጥና ወይንም ስለ ግንደ ቆርቁር የግንድ ኣሰራሰር ኣንተ ነህ በሚዲያው የምትጠራው:: ኣንዱ ሚዲያ ኢንተርቪው ያደርግህና ለዛኛው ሚዲያ ያቀብሉሃል ማታ ደግሞ ፓልቶክ የክብር እንግዳ ተብለህ ትገኛለህ:: እውነቱን እንነጋገር ከተባለ የኢትዮጵያን የፖሎቲካ ሂደት ለማየትና ኣስተያየት ለመስጠት የፖሎቲካ ሳይንስ ምሁር መሆንንን ኣይጠይቅም ወይንም ደግሞ ዶክተር መባል ግድ ኣይልም:: ስለ ኬምስትሪ ፊዚክስ ለማውራት ስለ ጂኦሎጂ ወይንም የከርሰ ምድር ጥናት ኣስተያየት ለመስጠት ምሁራዊ ብቃት ግድ ይላል:: የፖሎቲካ ጉዳይ ለመትንተን ቀናነትና መልካም ኣሳቢነት እንጂ ዶክተርነትን ኣይጠየቅም ለምን ቢባል በየቀኑ በሁሉም የስሜት ህውሶቻችን የምንዳሰሰ ው ያገራችንን የእ ለት ውሎ ነውና:: ታላቁ ደራሲ በኣሉ ግርማ እንደሚለው “ደራሲ ለመሆን የሚያስፈልገው ትልቅ ድር ሰት እንጂ ከታወቀ ዩኒቨርስቲ መመረቅን ኣይደለም “” ::
ያገራችንም የፖሎቲካ ጉዳይም እጃችን ላይ ያለ እንቁላል ነው ዶክተር ዶክተር እከሌና ፕሮፊሰር እከሌ ሊነግሩኝ ኣይገባም እናም እነዚህ ዶክተር ብላውና ውቃው ካለባቸው የጊዜ ጥበት ስለተገኙልን እናመስግናቸዋለን ተብሎ የሚሰጡት ትንታኔ የሚይስቅም የሚያሳዝንም ነው:: ኣንዳንዶቹ ባዲስ ኣበባ ዙሪያ የተፈጠረው ያለመግባባት ችግር የኣብዮት መጀመሪያ ነው ብለው ደምድመዋል :: ከንግዲህ ወደፊት እንጂ ወደ ሗላ ማለት የለም “የመዘዝከውን ጎራዴ ወደ ሰገባው ኣትመልሰው” ኣይነት ሳጥናኤላዊ መልክታቸውን በስፋት ይሉታል ራሳቸውን የፍሊሚያው ኣስጀማሪ የጥይት ኣስተኴሽ በማስመሰል…lol ህዝብ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞውን መግለጽ መብቱ ነው ያልተመቸውንና ያላመነበትን ወይንም ያልመከበረበትን በሰላማዊ ቅ ዋ ሜ መግለጹ ሊያስወቅሰው ኣይገባም :: በዛ ብዥታ የለብኝም:: ግን በተቃውሞ ስም መንግስት ለምኖም ሆነ በርዳታ ጠይቆ ያገኘውን ኣምቡላንስ መስበር ህዝቡ ለልጆቼ ማሳደጊያና ማስተማሪያ ይሆነኛል ብሎ ኣክሲዮን በመግዛት ያስቀመጠውን ብር መዝረፍና ባንኮችን ማቃጠል ያካባቢውን ህዝብ በመለወጥ ላይ ያሉትን የኢንቨስተሮችን የእ ርሻ ቦታ በግማሽ ሰኣት ውስጥ በሰደድ እሳት ማውደም እንዴት ተብሎ ነው ሰላማዊ ተቃውሞ ነው የሚባለው?? የጸጥታ ሃይላትን እስከ መግደል ድረስ መሄድ እጅና እግራቸውን የፊጥኝ ከነ ኢኒፎርማቸው ኣስሮ የተመዘዘ ቢላ ይዞ በፌስ ቡክ ፎቶ ላይ መለጠፍ እንዴት ሰላማዊ ተቃውሞ ያስብላል?? ከላይ ያነሰሗቸው “ ጭር ሲል ኣልወድም ዶክተሮች” ስለዚህ ነገር ምንም ሳይሉ ሰላማዊ የሆነውን ህዝብ በሰላም ወጥቶ መብቱን ሲጠይቅ መንግስት (ያው እነሱ መንግስት ኣይሉም ሁሌም ያ የፈረደበት ወያኔ ነው የሚሉት) “ በሄሊኮብተር በተጠመደ መትረየስ ፈጃቸው” ይሉናል :: ለዳንጎቴ የሲምንቶ ፋብሪካ ውድመት ወይንም ምርጥ ዘር በማዳቀል በመላው ያገሪቱ ክፍል ለማከፋፍል ላለፉት ኣራት ኣመታት ሳይታክት ሲደክም የነበረውን ና ውጤቱን ለህዝብ ለማቅረብ በመጨረሻው ሰኣት ላይ ስለሚገኘው የደች ኣግሮ ካምፓኒ በሰደድ እሳት ማውደም ኣንድም ነገር ትንፍሽ ኣይሉም:: ህዝብ መብቱ ነው ይሉሃል ያገር ሃብትና ንብረት እያወደምክ መብ ቱ ነው ማለት እንዴት ነው?? ኣንድ መንግስት እኮ ዘላለማዊ ኣይደለም ሀገር ግን ዘላለማዊ ናት:: የፊንጫን ሃይድሮ ኤለክትሪክ ግድብ ያሰሩት ጃንሆይ ናቸው ጃንሆይን ያሰውገዳቸው ደርግ ግን እሳቸው ባሰሩት ግድብና መብራት ይጠቀም ነበር:: ይሄንን ቅድም ያልኴቸው ስለ ስለ ቅጠል ኣበጣጠስ ወይንም የጉንዳንን ኣኗኗር ኣጥንተው ፒ ኤ ች ዲ ኣቸውን የሰሩት ዶክተሮች ለህዝ ቡ ኣይነገሩትም:: ሌላው የሚገርመው ጉዳይ በሰሙኑ ጉዳይ ኣማራና ኦሮሞ ኣንድ ሆኖ ከቆመ ወያኔ መቀበሪያዋ ደርሷል የሚሉት ነጠላ ዜማቸው ነው:: ለመሆኑ ኢትዮጵያ ያማራና የኦሮሞ ብቻ ናት እንዴ?? ትግራይ ኢትዮጵያዊ ኣይደለም ? ሃመር ጉምዝ ስልጤው ኣፋር ሱማሌ ጋምቤላ ቤንሻ ንጉል በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ምንም ለውጥ የማያማጡ የዜሮ ድምር ናቸው ማለት ነው ?? አነዚህን ሳስብ ዶክትሬት ለማጥናት እያሰብኩ ነበረ ግን ኣሁን ሳልተወው ኣልቀርም መሰለኝ lol ሰላም ሁኑልኝ ::
ዜናዎቻችን በተከታታይ እንዲደርሷችሁ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ “Like” ወይም “Comment” ወይም “Share” ያድርጉ!!

https://www.facebook.com/pages/Ethiopian-This-Week/114125298610656?pnref=story

 

 

እየተስተዋለ ጎበዝ … ሽብርተኝነት “ኣፍሪካና ኣውሮፓ” እያለ ኣይለይም

ስለ ፓሪስ እልቂት ስናስብ በኬንያ ዩኒቨርስቲ የተቆሉትንም ኣብረን እናስብ :: እነዚህም ኣንድ ኣይነት ኣመለካከትና ኣስተሳሰብ ባላቸው እኩያን እየተለቀሙ የተቆሉ ናቸው!!! ችግሩ ኣገራዊ ሳይሆን ኣህጉራዊ ነው ያልተነገረላቸው ያልተጻፈላቸው ሚዲያ ያልጎበኛቸው ቡዙ ነፍሳት በ ኣይ ሲስ በዳሽ ባልካይዳና ኣልሸሽባብ ጥይትና ካራ እየተሰው ነው:: ኢራቅ ይሄ ችግር ኣለባት… ሲሪያ ይሄ ችግር ኣለባት… ኣፍጋንስታን ውስጥ ይሄ ችግር ኣለ.. ካሽሚር በ እምነታቸው ምክን ያት ዜጎች የሚታረዱባት ኣገር ናት:: ቦክሃራም ናይጄሪያ ውስጥ infidels ወይም መናፍቅ እያለ ቡዙዎችን እያረደ ነው:: ጎረቤታችን ሱማሊያ ይሄ ችግር ኣለ እኛን ይሄ ችግር ኣይመለከትንም ማለት የዋህነት ነው በኢትዮጵያ የደህነነት ሃይሎች ጥንካሬ ቡዙዎች ተመክተዋል:: ሽብር ግን የፊት ለፊት ውጊያ ኣይደለም ባልተጠበቀና ባልታሰበ ሰ ኣት ሊከሰት የሚችል ነገር ነው:: ባለፈው የኢትዮጵያና የናይጄሪያ ጨዋታ ሲካሄድ እጅግ ኣሰቃቂ ኣደጋ ሊከሰት ይችል ነበር… ኣፈንጂዎቹ ራሳቸው ፈነዱ!!!
እንደተባለው ሁላችንም ዙሪያችን ኣካባቢያችንን መጠበቅ ኣለብን በጣም የተቀናበረ ወይም ኮርዴኔትድ የሆነ መረብ ባለማችን ላይ ኣለ ቦኮሃራም ያለ ሽብርተኛ ካይሲስ መመሪያ ይወስዳል … ሱማሊያና ሊቢያ ውስጥም የኣይሲስ ኔት ( network ) ኣለ ችግሩ የሁላችንም ነው:: ኣለም ኣንድ ሆና መቅረብ ኣለባት:: ሃያላን መንግስታት ራሳቸው ከዚህ ኣላመለጡም!! ዛሬ በፈረንሳይ የሆነው ነገ በ እ ንጊሊዝና ባሜሪካ የማይሆንበት ምንም ምክን ያት የለም ካሜሪካ ከከናዳ ከእንጊሊዝ እ የሄዱ ኣይሲስን የሚቀላቀሉ ወጣቶች ኑሮ መኖር ኣቅቷቸው ወይም ተቸግረው ወይም በገንዝብ ተታለው ኣይደለም:: በሶሻል ሚዲያ በሚሰጣቸው ቅስቀሳ በማመን ነው ጀሃዲ ጆን የሚባለው የሰው ኣንገት በመቅላት እርካታ እንደሚያገኝ በይፋ የሚናገረው ለንደን ከተማ ውስጥ ከቤተሰቡ ጋር በምቾት ነበረ የሚኖረው ነገር ግን እሱም ራሱ በሶሻል ሚዲያ ኣማካይነት ነው ኣይሲስን የተቀላቀለው:: እርሱ ራሱ ኣንዱ ተጨማሪ ስራው በፌስ ቡክና በቲውተርስ ወጣቶችን ወደ ኣይሲስ እንዲገቡ መቀስቀስ ነበረ:: ኣሸባሪዎችን ለማጥፋት እነዚህን ቦታዎች ሁሉ መሸፈን ያስፈልጋል ከ እስልምና እምነት ውጭ ዶክትሪን የሚያስተላልፉ ወይም የሚያስተምሩ የእምነቱ ኣስተማሪዎች ታርጌት መደረግ ኣለባቸው:: ችግሩ እነ ኣሜሪካ ምን ያህል ቁርጠኝነት ኣላቸው?? የሚለው ነው ኣይሲስ ክርስቲያን ወይም የሌላ እምነት ተከታይ ስለሆነ ብቻ ኣይገድልህም ቡዙ የሙስሊምእምነተ ተከታዮች ራሳቸው እንደ በግ እየተጎተቱ ታርደዋል.. በጥይት ጭንቅላታቸውን እየተመቱ ተገድለዋል::
ዶክትሪያናቸውን ማወቅና ማጥናት ይሄንንም የሚያስተላፉበትን ስትሪም ( stream) በሚገባ ፈልጎ ማግኘት ያስፈልጋል:: እኔ በጆሮዬ አዚህ ኣሜሪካ ኣገር በሚተላለ ፍ ሬድዮ ኣንድ የሙስሊም ኣስተማሪ ነኝ የሚል ሰ ው በሳምንታዊ የሬድዮ ፕሮግራሙ “ኣላህ ደም ይወዳል ደስም ይለዋል… ጦርነት ሲኖር ፈረሶች እየጋለቡ በኮቴኣቸው ከመሬቱ ጋር እየተጋጩ እሳት ሲፈጥሩ ኣላህ ደስ ይለዋል..” ሲል ሰምቻለሁ ይሄን የተቃወሙ ሙስሊም ወዳጆች ኣሉኝ የተቀበሉም ኣሉ:: በእነደዚህ ኣይነት ሁኔታ ነው የሰውን ልብ እየሰለቡ ( Brainwash) እያደረጉ ያሉት ::
ኣይሲስ በዚህ ረገድ እርዳታ የሚሰበስበት ወጣቶችን ባለም ዙሪያ የሚቀሰቀስበት በደንብ ኮርዴንትድ የተደረገ ኔት ዎርክ ዘርግተዋል ከተለያየ ያለም ክፍልም fund ኣላቸው የ ራሳቸው የነደጅ መውጫም ኣላቸው ሲሪያ የነበረውን ራሽያ ኣውድመዋለች:: በኢራቅ ግን ትልቅ ሪሶርስ ( Resource ) ኣላቸው:: ሱኒዎች ነን በሚል ስም ከሳውዲያና ካንዳንድ ሃብታም ኣገሮ ች እርዳታ በሚስጥር እንደሚደርሳቸው ይነገራል ::አናም ችግሩ ኣካባቢያዊ ወይንም ያንድ የሁለት ኣገር ጉዳይ ሳይሆን የ እያንዳንዳችንን ቤት እያንኴኴ ያለ ችግር ነው::

ቡዙ ጊዜ በፌስ ቡክ ከማገኛቸው የሚያስቁ መልእ ክቶች ኣንዱ “እከሌና እከሌና የሚባሉ የፌስ ቡክ ጏደኞችህ ዛሬ የልደት ቀናቸው ነውና መልካም መልእክት ተመኝላቸው ወይም የመልካም ምኞት መግለጫ ላክላቸው” የሚለው ጉዳይ ነው::

እነዚህ የማውቃቸው የፌስ ቡክ ወዳጆቼ እውነተኛውን የልደት ቀናቸውን ማክበር ካቆሙ ዘመናት ኣልፈዋል..lol እኔን የገረመኝ (እናንተንም ሳይገርማችሁ ኣይቀርም ብዬ ኣስባለሁ) ባለቤቱ እያለ “ልደታቸውን ኣክብሩላቸው” እያለ ፌስ ቡክ ራሱን ለምን ያጨናንቃል?? ዕኛንስ ለምን ይነዘንዘናል? ስንት ቁም ነገር መሰራት እየተቻለ እያልኩ ነው :: ኣንዳንዱ (እኔንም ጨምሮ) የልደት ቀኑን ሲያስብ ልብ ድካሙ ሊቀሰቅስበትም ይችላል እኮ..lol

ኣንድ ወዳጄ ከሚኖርበት ከተማ በዛ ሰሞን ደውሎልኝ “ዛሬ የልደት ቀኔ እኮ ነው” ብሎ ኣዝኖ ነገረኝ ..”

ታዲያ ደስ ይላል ኣጠገብህ ብሆን ኖሮ ወደ ከተማ ወጣ ብለን ወይን ጠጅ እንጎነጭ ነበረ ባንተ ሰበብ እኔም የመጠጥ ጾሜን እፈታ ነበር” ብዬ ቀለድኩ:: ወዳጄ ግን ቀልዴ ኣላሰቀውም.. “እባክህ ተወኝ ለካ በዚች ም ድር ላይ ይሄን ያህል ኣመት ኖሬኣለሁ ያንን ኣላውቅም ነበር ምን ቀረኝ ህይወቴን እኮ ኣጋምሸዋለሁ!!´ ብሎ የባሰ ተከዘ

“መፍትሄው የትናንቱን ሳይሆን ነገ ኣዲስ ቀን ነው ነገን ምን ጥሩ ነገር ልስራበት ብሎ ማሰብ ነው”” ብዬው ተለያየን::

ምን ይላሉ ወዳጄ?? ትክክል ኣላልኩም??

ዜናዎቻችን በተከታታይ እንዲደርሷችሁ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ “Like” ወይም “Comment” ወይም “Share” ያድርጉ!!
https://www.facebook.com/pages/Ethiopian-This-Week/114125298610656?pnref=story

አርስዎ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ?”
( አስገራሚ የባል ኑዛዜና አስደናቂው የሚስት ምላሽ ያንብቡ ይገረማሉ። )

አንድ ከምንም ነገር በላይ ገንዘቡን አጥብቆ የሚያፈቅር ባለጸጋ ሰው ከመሞቱ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ ለሚስቱ የሚከተለውን ቃል አስገባት ” የእኔ ውድ የመሞቻዬ ቀን ታውቂያለሽ ስለዚህ እጅግ አድርጌ የምወደውን ገንዘቤን በሳጥኔ ውስጥ አብሮኝ እንዲቀበር ታደርጊልኝ ዘንድ ቃል ግቢልኝ” ይላታል።

ሚስቱም ባሏን አክባሪና አፍቃሪ ነበረችና ገንዘቡን በሙሉ አብሮት እንዲቀበር እንደምታደርግ ቃል ገባችለት። በዚሁ መሰረት ባሏ ይሞትና በሬሳ ሳጥን ውስጥ ” ገንዘቡ” በአንድ ሳጥን አብሮ እንዲዘጋበት በማድረግ ወደ ጉድጓድ ይገባል።

ይህንኑ የሴቲቱ ድርጊት የተመለከተችው የባልዬውን ኑዛዜ የምታውቅ ጓደኛዋ የተመለከተችውን ነገር ማመን ይሳናታል። ” አንቺ መቼም ከባልሽ ጋር ገንዘቡን በሳጥን አድርገሽ እስከ መቅበር የሚያደርስ ሞኝነት ይዞሻል የሚል እምነት የለኝም ካላበድሽ በስተቀር ከነ ገንዘቡ አትቀብሪውም፡፡ ለመሆኑ አብረሽ ቀበርሺው እንዴ? ” በማለት በአግራሞት ትጠይቃታለች።

ሚስትዬዋም ” ስሚ አንቺ እኔ እኮ የእምነት ሰው ነኝ ቃሌንም በማጠፍ የባሌን ነፍስም ፈጣሪንም አላሳዝንም ቃል በገባሁት መሰረት ገንዘቡ በሳጥኑ ውስጥ አብሮት እንዲቀበር አድርጌያለሁ፡፡” አለቻት።

ጓደኛዋም መገረምና አድናቆቷ ጨምሮ “እና ገንዘቡ ሁሉ ሬሳ ሳጥኑ ውስጥ ጨምረሽ ከእሱ ጋር ተቀብሯል” በማለት በድጋሚ ጠየቀቻት።

ሚስትየዋም ” ከገንዘቡ አምስት ሳንቲም ሳላጎድል ከእሱ ጋር አብሬ ቀብሬዋለሁ። በእርግጥ ጥሬውን ሳይሆን ቼክ ነው የጻፍኩለት” አለቻት።

እንግዲህ ሚስትዬዋ በቼክ መጻፏ እውነቷን ነው ቼኩን በሰማይ ቤት የመመንዘር ያለመመንዘር ውሳኔ የባሏ ነው። በሰማይ ደግሞ የሚመነዘረው ቼክ ሳይሆን በምድር የሰሩት ደግ ስራ ነው።
እርስዎስ ምን ይላሉ? አስተያዬት ይስጡ፡፡
ምንጭ፦ “የፍርሐት ካቦች” በሚል ሐይለጊዮሮጊስ ማሞ ከጻፈው መጽሐፍ የተወሰደ ነው።

ዜናዎች በተከታታይ እንዲደርሳችሁ ድህረ ገጻችንን መጎብኘት ኣይዘንጉ ወይም ስብስክራብ ( subscribe ) ያድርጉን:: Our web site address is http://www.ethiopianthisweek.com/ or contact is at ethiopianthisweek@gmail.com

Thanks,

ETW Editor

ይሄን ፎቶ ስመለከት የታዘ ብኩትን ጀባ ልበላች ሁ ኪይ ቦርድ ተጫዋቹና ጊታር መቺው በቅኝት የተገናኙ ኣይመስለኝም ምስሉን ይመለከቱት እንደውም ሳክስፎን ተጫዋቹ በመሃል ባይገባ ና “ኣንተም ተው ኣንቺም ተይ” እያለ ባያንጎራጉር በካራቴ ኣይሞካከሩም ነበረ ትላላች ሁ lol ኪይ ቦርድ ብቻውን ባንድ ( Band ) በሆነት ጊዜ ላይ ስለደረስን ከሌሎች ባለሙያዎች ጋር ተዋህዶ መስራት ችግር እየሆነ መምጣቱን በሙያው የተሰማሩት ባለሙያዎች የሚያነሱት ነው :: ቡዙ ጊዜ ባለሙያዎቹ እንደሚሉት ቴክኖሎጂ ስራቸውን እንደቀማቸው ይናገራሉ እኔ እንደውም ኪነ ጥበባዊ ችሎታቸውንም ኣብሮ ዘመነኛው ኪይ ቦርድ የዘረፋቸው ይመስለኛል የኪይ ቦርድ መኖር ኪነ ጥበብን ኣሳድጔል ወይስ ባለሙያዎችን (ሳክሲፎኒስት ጊታር ተጫዋቾችን ) ከመድረክ ኣሽሽቷል ..? ምን ይላሉ..?

ኣንድ ወዳጄ መምህር ግርማ (እሱ ግን የሚጠራቸው መ ስ ህ በ ዛር ግርማ አያለ ) ነው እና እኝህ የደሩ የኮሩ ኣባት የቅልጥጤ ኑሮ ነው የሚኖሩት ኣለኝ ካላመንክ የመኖሪያቸው ቤት ዋጋ ሀብተ ፈውስ እንዳላቸው ደገኛ አባቶች በዐጸደ ቤተ ክርስቲያን በመንፈሳዊ ተጋድሎ ተወስኖ ሳይሆን በ፩።፭ ሚልዮን ብር ወጪ የተገነባ መሆኑን ዛራ ዘ ተዋህዶ ያወጣውን ዜና ፈልገህ ኣንብብ ኣለኝ እሪ በል ሽዋ ኣልኩኝና የዛሬውን ወጌን እንዲህ ስል ጀመረኩ ሰላም ነው ኣድባሩ በማለት…

እኔ የምለው ..መእምናንና መእ ምናት ለካ መምህር ግርማ ወንድሙ (ኣንዳንዶች መስህበ ዛር ግርማ ወንድሙ ይሏቸዋል ለምን እንደሆነ ኣላውቅም) ባለ ትዳርና የሶስት ልጆች ኣባት ናቸው:: ! እኔ እኮ ድንግል መነኩሴ ወይም የመነኑ ባህታዊ ይመስሉኝ ነበር… ለነገሩ በቁርባን ከሆነ ያገቡት ወይም ካገቡ በሗላም ከሆነ የቆረቡት ችግር የለውም:: ባለ ትዳር መሆን መንፈሳዊ ኣገልግሎትን ኣይከለክልም:: ግን ..ግን ፈተና የሚበዛበት ይመስለኛል ልጆች ፍላጎት ይኖራቸዋል …ወጪው ይበዛል… ባለቤት ደግሞ እቤት እሳቸውን ጥለው ኣገር ላገር ሲዞሩ “ ምነው ኣንድ ቀን እንኴን ከጎንዎ ኣድርገውኝ ቢታዩ ወይም ኣብሬ በርሶ ሰበብ ኢሮጵን ወይም የሩሳሌምን ተሳልሜ በመጣሁ …የሚል የሚል በጉጉት የተሞላ መንፈሳዊ ጥያቄ የሚጠይቁ ይመስለኛል….. መመህር ደሞ የበቃ ለመምስል ሚስታቸውን ይዘው መታየታቸው መንፈሳዊ መጎናጸፊያቸውን የሚያወርድባቸው መስሎ ታይቷቸው ይሆናል …ብቻ ግምቴን ነው የምሞነጫጭርላችሁ “ምንጭርጭር” ትል ነበር ኣንድ የድሮ የብእር ወዳጄ..lol

ነገርን ነገር ያነሳዋልና በህግ የተያዘው የመመህር ግርማ ጉዳይ ከሳምንት በሗላ ይለይለታል ተብሏል ሰውየው (ኣቶ በላይነህ ከሳ ሽ ማለት ናቸ ው ) ክሳቸው ሁለት ስለት ኣለው ነው የተባለው:: ኣንደኛው እቺን ቤት ለቀህ ካልወጣህ ሬሳህ ይወጣል የሚል ማስፈራሪያ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ 800 ሺውን to the power of 2 squared ላድርግልህ

ወይም ላባዝልህ ብለው ኣቀለጡኝ !! ነው የሚሉት kkk.. እስኪ ሁሉንም ኣብረን እንይ.. የነገም የከነገ ወዲያም ሰው ይበለን

ዜናዎቻችን በተከታታይ እንዲደርሷችሁ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ “Like” ወይም “Comment” ወይም “Share” ያድርጉ!!
https://www.facebook.com/pages/Ethiopian-This-Week/114125298610656?pnref=story

የዛሬው የማለዳ ወግ በመምህር ግርማ ወንድሙ ኣንጻር ቅኝቱን ያደርጋል

መል ኧክ መንክራት ግርማ ወንድሙ እውነተኛ ኣባት ናቸው ወይስ ማጅራት መቺ??
ኣንመጻደቅ ጎበዝ..!! ኣንድ ሰው የሓይማኖት ኣባት እንዲባል ከተፈለገ መጀመሪያ በቅድስና ሊመላለስ ይገባል:: ለመንፈሳዊ ልጆቹ ኣ ር ኣያም ሊሆን ይገባል:: መል ኧክ መንክራት ግርማ ወንድሙ ለምን ታሰሩ ?? ሲዘርፍ የተገኘ ኣባትን በቁጥጥር ስር ማዋል ከመንፈሳዊ ስደት ጋር ምን ያገናኝዋል?? ኣንድ ሰው ካባ ለብሶ ዘራፊ ከሆነ ጸጋን ከለላ ኣድርጎ ሊያመልጥ ይቻለዋልን?? የሰው ህግ ኣለ…. የእግዚኣብሄር ህግም እንደዛው ኣለ:: ለፍርድ የእግዚኣብሄር እጆች ኣይቸኩሉም ቢቸኩሉ ኖሮ መጀመሪያ የምጠፋው እኔ ነበርኩ ..ቀጥሎ ደግሞ ሊጠፉ የሚችሉት እርሶ ሊሆኑ ይችላሉ ውድ ኣንባቢ:: የሰው ህግ ለወንጀለኛ ኣረንጔዴ መብራት ኣያበራም ይሉቁኑ በቀይ መብራት ያስቆማል:: እጊዚኣብሄር ደሞ በራሱ ሰአት ይጠይ ቀናል አዚህ ጋ “800 ሺ ብር ቤቴን ኣስገድደው እንድሽጥ ኣድርገውኝ ከሽጥኩ በሗላ ደግሞ ገንዘቡ እንዲባዛ ልጸይበት ሳትነካው እንዳለ ኣምጣው ብለውኝ እኔ ደሞ ባባትነት ኣምኛቸው ከሰጡሗቸው በሗላ ስልካቸውን ሁሉ ዘጉብኝ የህግ ያለህ !!ያገር ያለህ!! የመንግስት ያለህ !!” እያለ የሚጮህ ምስኪን ኢትዮጵያዊ እያለ መምህር ግርማ የታሰሩት እጊዚኣብሄር በ አስር ቤት ድንቅና ታምራቱን ሊሰራ ስለፈለገ ነው እያሉ መመጻደቅ ምን የሚሉት እምነት ነው???? “የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ እኔና ቤቴ ግን እግዚኣብሄርን እናመልካለን” ይላል የእግዚኣብሄር ሰራዊት ጄኔራልና መሪ የሆነው ኢያሱ እኮ ነው:: “እውነተኛው መንፈስ ሳይመጣ ከሰማርያ እንዳትወጡ” ያለው ምን ማለት እንደሆነ የገባኝ ኣሁን ነው…lol የተባረከ ቀን ይሁን ::

እስኪ ከቁም ነገር ወጣ ብለን ትንሽ እንዝናና ፈገግ ታደርጋለች ወዲህም የምታስተላፈው መልእክት ይኖራል ብዬ ያሰብኩትን ኣንድ ቁም ነገርን በኣናቷ የተሸከመች ቀልድ ላካፍ ላች ሁ…..

ሰውየው እንግዲህ በየሳምንቱ ወደ ጸሎት ቤት እየሄደ ይንበረክክና ካምላኩ ጋራ በንስሀ ጸሎት ይነጋገራል :: እንዲህ እያለ …….

“” አቤቱ ቸሩ አምላኬ ሆይ ! በልቤ ውስጥ ድሩን ያደራውን የሀጢአት ድር እባክህን ጥረግልኝ !!!””

ይህን ካለ በኈላ ወደ ቤቱ ተመልሶ ሲሄድ ያንኑ ሀጢአት መፈጸሙ አይቀርም :: እናም በሳምንቱ ተመልሶ ይመጣል ::

እየተንሰቀሰቀ ….. ” አቤቱ ዘላለማዊ አምላክ ሆይ ….ይሄን በልቤ ያደራውን የሀጢአት ድር እባክህን አጽዳልኝ ::”

በሚቀጥለው ሳምንትም የሚጸልያት ጸሎት ይህችው ናት :: ከሚሰራው ሀጢአት ቆርጦ መለያየት አልቻለም :: ታዲያ አዘውትሮ ከጎኑ የሚጸልየው ሌላ መምእን የዚህ ሰው ተደጋጋሚ ለቅሶ ስላስመረረው ወደ ተንበረከከበት ጎንበስ ብሎ ……

” ሰማህ ወይ ወንድም …እንደው በየሳምንቱ ድሩን ከምታስጠርግ ምናለ ሸረሪቷን በፊሊት ብታስገድል??”

የህይወት ሚስጥር….

ኣንዳንዴ ወደፊት ሮጣችሁ ህይወትን እንዳታሽንፏት ያገዳችሁ ምን እንደሆነ ለማወቅ ኣስባች ሁ ታውቃላች ሁ?? ኣንዳንዶቻቹ የሰው ኣይን ነው ትሉ ይሆናል ኣንዳንድሽ ደሞ ተወኝ እባክህ ሲፈጥረኝ እድለ ቢስ ኣድርጎ ፈጥሮኝ ነው እያላችሁ እድላችሁን ዘውተር ትራገማላች ሁ… ኣንድ ወዳጄ “የወላጆቼ ከራማ እየተከተለኝ ነው “ ሲል እሰማዋለሁ ምን ማለት ነው? ብትሉት እሱም ኣይገባውም lol :: ሁሉም ግን ትክክል ኣይደለም ብታምኑም ባታምኑም ችግሩ ያለው ራሳችን ላይ ማለቴ ጭንቅላታችን ላይ ነው የፈረስ ያህል ጉልበት ኖሮን ሮጠን እንኴን ላለማምለጥ ወስጣችን የፈጠረው የተሽና ፊነትና ያለመቻል መንፈስ ሁለንተናችንን ተብትቦ ይዞናል!! ኣይንም, እድልም, ኣሽን ክታብም… ኣይደሉም የጠፈሩን :: ራሳችንን ያሰርነው ራሳችን ብቻ ነን:: እቺን ስእል ልብ ብለው ይይዋት እኔን ኣስተምራኛለች…!! እርግጠኛ ነኝ ለርሶም የምታስተላልፈው መልእክት ኣለ…

መንፈሳዊ መዝሙሮች ኮፒ ራይት ወ ይም የባለቤትነት መብት ኣይኖራቸውም??

ምናልባት ፈጣኑ ና ኣጭሩ መልስ ባለቤቱ ሰው ሳይሆን ፈጣሪ ራሱ ነው እነሱ ዘመሩት ወይም ኣዜሙት እንጂ ሲጀመርም የነሱ ኣይደለም የሚል ኣርግዩመንት( argument ) ሊኖር ይችላል:: ያስኬዳል… ግን እኮ ካሴቱን ይሽጡታል ሲሸጥም እኮ ገቢው ወደ ዘማሪዎቹ ኪስ እንጂ ወደ እግዚብሄር ካዝና ሲገባ ኣናይም::

ጠይና ይስጥልኝ ውድ ኣንባቢ ይሄን እንደ ማቆያ እንያዘውና ኣንድ በጣም በግጥምም በዜማውም ወደ ተመሳሰለብኝ ስራ ልውሰድዎ ይከተሉኝና ኣስተያየትዎን ሲመችዎ ጫር ጫር ያድርጉልኝ…

በታላቁ መጽሃፍ ተጽፎ እንደሚገኘው ልሳናት ሁሉ እጊዛኢብሄርን ያመስግኑት በዝማሬና በዜማ ያመስግኑት ይላል የተለያዩ ነገዶች ና ኣህዛቦች በቌንቋቸው የምስጋና ዜማን ላምላካችን ያዚሙም ይላል ኣንደበትን የፈጠረ የተላየየ ቌንቋ እንዲኖሩ ያደረገ የምስጋና መዝሙር ቢቀርብለት ቅር የሚለው ወይም የሚከፋው ኣንድም እንደርቢ የያዘው ሰው ነው ወይም የቃልቻ መጀን ነው ይሁን እንጂ ሰዎች እጊዚኣብሄርን የሚያመሰግኑት በውስጣቸው ከመነጨ ዜማ መሆን ኣለ በት ወይም በጸሎት ከተገኘም መገለጽ መሆን ይገባዋል:: የሌላውን በመኮረጅ ኮፒ( copy ) ማድረግ ያ እውነተኛ ምስጋና ኣይደለም:: የኮፒ ራይት ( copy right ) ጉዳይ ባለማዊ ዘፈኖች ብቻ ሳይሆን በመንፈሳዊ ዜማዎች ሊታይበትና ሊታሰብብበት ይገባል ..ወይንም ዜማውን ከወደዱት ወደ ኣንድ መጠቃለል ነው የ እ ግዚኣብሄር ኣባታችን ቤት እኮ ሰፊ ነው ይሄን ዜማ ስሙና በቀናነት ኣስተያተቻሁን ጻፉ:: መናፍቅነት ነው የሚለው ነገር እዚህ ጋ ላስተያየት ኣይመጥንም :: ካለብን የመንፈሳዊ ምርምር እጥረት( Spiritual insight ) ወይንም የመናፍቅነትን ትክክለኛ ትሩጉም ካለመረዳት የሚቀርብ የችኮላ ድምዳሜ ይመስለኛል:: ወደ ዝማሬው ልውሰዳችሁ…. በነገራችን ላይ ካልባረከኝ ኣልቀህም ያለው ያእ ቆብ የሚባለው የኣ ብርሃም ( Abraham ) ወይም የኢብራሂም ( Ibrahim ) ወይም የኤብርሃም ( Ebrahem) የልጅ ልጅ ነው በረከቱ በያላች ሁበት እንደ እምነታች ሁ ይድረሳ ችሁ ::
https://www.facebook.com/video.php?v=932209890147932

የፖሎቲካ ስደተኛና የኢኮኖሚ ስድተኛ ይለይ …

የሻ እቢያ መንግስት ላገሪቱ ዜጎች ማለትም ለኤርትራውያን ኣገርን ሳይሆን ትልቅ እስር ቤትን እንደገነባላቸው ለማወቅ በየቀኑ ካገሪቱ በመሬትም ሆነ በባህር እየኮበለሉ የሚሄዱት ኤርትራውያንን ቁጥር ማየት በቂ ማስረጃን ይሰጣል:: ኩብለላው ኣቶ ኢሳያስና ያስተዳደር መልህቃቸው በኤርትራ ምድር እስካለ ድረስ ማቆሚያ ኣይኖረውም ኤርትራውያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን መከራውንና ችግሩን ተጋፍጠው ገንዘብ ሳይሆን ህይወታቸውን ኣስይዘው ባገኙት ኣጋጣሚ በሩጫ ያችን ኣገር እየለቀቁ ይገኛሉ… ሳስበው ይህን ያህል ቁጥር ያለው ኤርትራዊ በየቀኑ ኣገሩን የሚለቅበት ምክንያትን ቆም ብሎ ኣስቦ በመሳበስብ ለምን ኣገሬን እንድጠላትና እንዳልኖርባት የሚያደርገኝን ስርኣት ኣልጋፈጠውም?? ብሎ ማስብ ኣይጀምርም እላለሁ:: ሽስተው ያመለጡት ግፍና ሞት መከራና ችግር ኣፉን ከፍቶ ድንበር ተሻግሮ በሊቢያና በሱዳን በረሃ ቀጠሮ ይዞ ይጠብቃቸዋል ይሄን ያህል ቁጥር ያለው ኤር ትራዊ በየቀኑና በየሳምንቱ በድንበር በኩል ሞትን እየዘለለ ከመውጣቱ በፊ ት ዞር ብሎ ወደ ሗላ በማየት እንደ ኣርማጌዶን ክንፎቹን በኤርትራ ተራሮች ላይ የዘረጋውን መንፈስ ባንድም ሆነ በሌላ መንገድ መተናነቅ መጀመር ያለበት ይመስለኛል:: የ ስደተኞችን ጉዳይ የሚከታተለው ጽ ህፈት ቤት በሚያወጣው መረጃ በየወሩ 7 ሲ ይህል ኤርትራውያን ኣገራቸውን እየለቀቁ ይገኛል ስሌቱን በኣመት ኣብዙት ከ 80 አከ መቶ ሽ የሚደርስ መስራት የሚችል ሃይል ይቺ ኣፍሪካዊ ኣምሳል ያላት ሰሜን ኮርያዊት ኣገር ታጣለች: ይህም አንግዲ ሞትን ኣሽንፎ ወይም ኣታሎ የወጣውን ብቻ ስናሳለው ነው በርግጠኝነት ለመናገር ሁኔታው ላቶ ኢሳይስና ክበባቸው መልካም ኣጋጣሚ ነው:: የሚቃወማቸው ዞር ብሎ በእምቢተኝነት በህዝባዊ ኣመጽ ወይንም Civil disobedience በመፍጠር ከመቃወም ይልቅ ጥሎላቸው ይወጣል ይሄም መኝታችውን ያሞቅላቸዋል እንጂ የሚያመጣባ ቸው ኧንዳችም ስጋት ከቶም ኣይኖርም!! ካንድ ወይንም ከሁለት ኣጋጣሚ በስተቀረ ኤርትራ ውስጥ ኣመጽ መደረጉን ወረቀት መበተኑን ሰላማዊ ሰልፍ መጠራቱን ወ. ዘ .ተ የምትሰማበት ኣጋጣሚ የለም:: የተያዘው በሩጫም ይሁን በብስክሌት ባለ ው ኣጋጣሚ ብቻ መሸሽ ነው…መሸሽ..መሸሽ…መሸሽ…!!! ይህንንም በማስብ ነው የጉዳዩ ዋና ሰለባ የሆነችው ኣገራችን በሸመልድባ ና በተለያዩ ቦታዎች የስድተኞች ጣቢያን በመክፈት ኣቅሟ የቻለውን ያህል ኤርትራውያንን በማስተናገድ ደፋ ቀና የምትለው:: ከዛም ኣልፎ የኣውሮፓ ህብረት ዘላቂ መፍትሄ ከመፈለግ ወይም ካካባዊው ኣገሮች ጋር በመሆን ከማፈላለግ ይልቅ እንደ ሶርያና ኢራቅ ስደተኞች ለኤር ትራ ስደተኞችም ወደ ኢሮጵ እንዲገቡ ኣረንጔዴ መብራት ያበራላቸው!! ሁኔታው ለጊዜው መፍት ሄ መስሎ ቢታይም እየቆየ ግን ኣገሪቱን በሰው ሃይል እንድትድሀይ ከማድረግና ለሻቢያም የሰላም እንቅልፍ ከመስጠት ባለፈ ዘላቂነት ያለው መልስ ኣይሆንም:: መፍትሄው ወደ ተራራው በመዞር ችግሩን ተጋፍጦ ዘለቄታዊ ሰላም የሚፈጠርበትን ማመቻቻቱ ላይ ነው:: ኤርትራውያንም ራሳቸውን በማደራጀት ወንድሞቻቸውን በየቀኑ የሚያብርራቸውን ስር ኣት ራሱን ለማባረር ስራ መስራት ይኖርባቸዋል መሽሽ ጊዜያዊ እንጂ ዘለቄታዊ መፍትሄን ኣያስገኝም::
በዚህ ኣጋጣሚም ኣገራችንም እንደ ሌሎች ኣገሮች የኢኮኖሚና የፖሎቲካ ስድተኞችን መለየት መጀመር ያለባትይመስለኛል:: ስንቶቹ ናቸው በርግጥ ያቶ ኢሳያስን ኣስተዳደር ተቃውመው ወይም ጠልተው ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡት?? ስንቶችስ ናቸው የኢኮኖሚው ሁኔታ የተመቻቸ መሆኑን በማየት ለተሻለ ኑሮ የሚመጡት?? ይህን የምልበት ምክን ያት ስላለኝ ነው:: ሰሞኑን የኣንደኛ ዲቪዚዮን የብስክሌት ተወዳዳሪዎች ድንበር ጥሰው ወደ ኢትዮጵያ የመግባታቸውን ዜና ሳነብ የተሰጠው ምክንያት ስላስገረመኝ ነው… ዜናው ላይ እንደሚለው ብስክሌተኞቹ ካገር እንዲወጡ የተገደዱት ዋናው ምክንያት ለመወዳደሪያ የሚሆን ኣዲስ ብስክሌት ስላልተገዘላቸው ነው ቢገዛላቸው ኖሮስ??? ኤርትራንም ኣይለቁም ለሻ ብያም ባንዲራቸውን እያውለበለቡ ኣይዞህ ከጎንህ ነን ይሉት ነበር ማለት ነው !! ታዲያ ይቅርታ ይደረገልኝና እነዚህንም ፖሎቲካዊ ስደተኞች ናቸው ብላ ኣገራችን መቀበል ኣለባት ?? መልሱን ላንባቢ እተዋለሁ ክቡራን ነኝ for more ..
ያስሩ ተጫዋቾች ዜና ቀለሙ ሳይደርቅ 7 ብስክሌተኞች ደግሞ ተጨመሩ:: ክንዷ ለስድተኞች ሁሌም የተዘረጋው ኣገራችን እንኴን በሰላም መጣች ሁ ብላቸዋለች ዝርዝሩ እነሆ

http://www.ethiopian-this-week.com/2015/10/seven-eritrean-cyclists-flee-to-ethiopia.html

የትእቢት መጨረሻው እንጦርጦስ ነው………

ዛሬ የታዘብኩትን ላዋይዎ … ባለፈው እንዳልኩዎት ትዝብቴን በብእር ቀርቼ ( መቅራት ) ካላስቀመጥኩት ይተናል :: ነገ የራሱ የሆነ ሌላ ግራሞትን ና ትዝብትን ይዞ ይመጣል :: ህይወት የዐጋጣሚዎች ስብስብ ብቻ ሳትሆን የትዝብትና የግርምት ድምርምር ውጤት ናት ብልዎት ትክክል ይሆን ? ብቻ እኔ የመሰለኝ ነው …ለዛም ይሆናል ቅዱሱ መጽሀፍ ለነገ አትጨነቅ ነገ የራሱ ጭንቀት … የራሱ የሆነ ሁከት አለው የሚለው …እውነት እኮ ነው ምን ይታወቃል ነገ የሚሆነው ..! የኮሌጅ ተማሪ እያለሁ …ሀይ ስኩል የነበሩ ጔደኞቼ የሚሰጡኝ አክብሮት ነበር :: ታዲያ እኔ እቺን ነገር “ሴንስ ” ማድረግ ጀምሬአልሁ በነገራችን ላይ በዚች ቃል አንዱ ፍንድቅድቅ በዚህ አባባሌ ሰሞኑን ሲፈነድቅ ነበር :: ሞኝ ተረቱ አልቆ ከተነገረ በኈላ ሰው ሁሉ ስቆ ሲጨርስ እሱ መሳቅ ይጀምራል ይሉኝ ነበር …መምህሬ ይሄይስ :: እና ወደ ጉዳዬ ልውሰድዎና ሻይ ቤትም ሆነ አንዳንድ ቦታም ከነዚህ ጔደኞቼ ጋር ሆኜ መታየትን እመርጣለሁ ..አርቲ ቡርቲውን ስናወራ አንዳንች ሌላችንን ባናከብርም ቁም ነገር ያለው ነገር ሲጀመር ግን ለኔ የሚሰጠኝ ለየት ያለ ክብር አለ :: ቀስ በቀስ ጫጫታው በረድ ሲል ይታወቀኛል እንደ ቀረበልን በራድ ሻይ አይነት :: ይቺ ነገር የልብ ልብ ሰጠችኝ :: ኩራትም ድፍረትም ወኔም ፈጠረችልኝ ;; ታዱያ ይሄን አልጠላሁትም :: እንደውም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየወደድኩት መጣሁ …ከበፊቱ የተሻልኩ ሆኘ ለመገኘት አዲስ ነገር ይዤ በየሳምንቱ ብቅ ማለትን አዘወተርኩ :: ቀስ እያልኩም ራሴን በነሱ ውስጥ ማየት ጀመርኩ :: አስተሳሰቤና አእምሮዬ በነሱ ተቀረጸ :: ምን አለፍችሁ የራሴ ሳልሆን የነሱ መሆን ጀመርኩ :: አዲስ ነእር ይዤ ብቅ ስለ የሻይ ፌሽታውም የዛኑ ያህል እየበረከተልኝ መጣ :: ይሄ ነገር ግን የኌላ ኌላ ችግር ይዞ አስከተለ :: እነሱ ከሚሰጡኝ አስተያየትና ግምት በመነሳት ሁሉንም ነገር አውቃለሁ የሚል የንቁራሪት አይነት እብጠት ውስጤ ተጸነሰ :: በተለይ አንደኛው ልጅ ሲሸረድደኝ ይሁን ከምሩ እስካሁን አላውቅም ( እምበርሀን ብቻ ናት የምታውቀው ) ምን አለኝ …አንቺ እኮ መጽሀፍ ላይ ስምሽ የለም እንጂ አባቴ ይሙት ፈላስፋ እኮ ነሽ …ብሎኛል :: ዛሬ ያ አብሮ አደግ ጔደኛዬ በህይወት የለም :: ቢኖር ኖሮ በጠየኩት ነበር :: እንደዚህ አይነት አስትያየቶች አሉታዊም አንቱታዊም ገጽታዎች አሏቸው :: ፈረንጆች “ፕሮስ አንድ ኮንስ ” ይሏቸዋል ..አስማታዊ ትርጉም :: ጥሩው መልኩ ተደማጭ ለመሆን በየጊዜው አርስትን ለማዘጋጀት ማንበብ አዳዲስ ነገርን መፈላለግ መጠየቅን ስለሚሻ እግረ መንገዱንም የእውቀትን አድማስ ያሰፋል :: መጥፎው መልኩ ደሞ ራስን አዋቂና ሊቅ አድሮጎ የማየት ሌላውን ወደ ታች የመመልከት ከኔ በላይ ማንም የለም አይነት ስሜትና ወደ ላይ የመንጠራራትን አባዜ ይፈጥራል :: በዚህ አይነት ህብረተስብ ውስጥ ኖረውና አድገው አካባቢአቸው ከፈጠራቸው ትንሽ ኩሬ ውስጥ ወጥተው ትልቁ ውቅያኖስ ዘው ብለው ሶቶ መሪና የገቡ አሉ :: “ካሊቢሬት ” ሳይደረጉ :: “ካሊቢሬት ” = “ሳይጠረቡ” :: አሁንም አስማታዊ ትርጉም :: እነዚህ ሰዎች ታዲያ በትልቁ ባህር ውስጥ የሚኖሩት ኑሮ ሰላም ያለው አይደለም :: ያኔ በትንሿ ምንጭ ውስጥ እያሉ ተሰሚ እንጂ ሰሚ ስላልነበሩ አውሪ እንጂ አድማጭ ሆነው ስለማያውቁ ሌላው በሰላም ሲዋኝ እነሱ ይደፈቃሉ :: ሲመቻቸውም ይደፍቃሉ :: ውድ አንባቢዬ ሆይ ይሄ ሊሆን የሚችል ክስተት ነው :: ባህሪያችንን የሚወስነው የየኖርንበት ማህበረስብ ነው :: በርግጥ ለመሰራታዊው ሰዋዊ ባህሪያት ቤተሰቦቻችን የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ :: ለማህበራዊ ግንኙነት ግን የተማርንበት ትምህርት ቤት , የህይወት ልምዳችን , ያለፍንበት ጉዞ , ጕደኞቻችን ለኛ ያላቸው አመላከከት እኛ ለነሱ የምንሰጠው አስተያየት ወ .ዘ .ተ አሁን ለምንኖርበት ኑሮ ተዋጽኦች ናቸው :: ትምህርት ብቻውን ማንነትን አይቀርጽም :: ባለ ድግሪ ሆኖ ንፍጣም አለ :: ሳይማር ደሞ ትሁት , መልካም ብሩህ አስተሳሰብ ያለው በማህበራዊ ህይወት ውስጥ ከሰዎች ጋር መኖር ምን ማለት እንደሆነ በትክክል የገባው አለ :: መማር ማለት ራስን መግዛት ነው አጉራ ዘለልነት አይደለም :: ኮለኔል መንግስቱ ሀ /ማርያም ስልጣን ላይ ሲወጡ ዐገር ወዳድ ለውጥ ወዳድና እድገት ለማምጣት ቆርጠው የተነሱ የሌሎችን ሀሳብ በጽሞና የሚያደምጡ ናቸው ይባል ነበር :: ትንሽ ቆይቶ ግን እርሶ የኢትዮጵያ ብርሀን , የኢትዮጵያ ሻማ የኢትዮጵያ ጧፍ , የኢትዮጵያ ነዶ , የኢትዮጵያ ስንደዶ , የኢትዮጵያ ጥቁር አልማዝ እንዲሁም ኢንዲሚክ ወፍ ( Endemic Bird) ነዎት የሚሉ ሰዎች በዙሪያቸው በረከቱ :: ይባስ ብሎ ከጎአድ መንግሱት አመራር ጋር ወደፊት የሚባል መፈክርና ጔድ መንግስቱ መንግስት ናቸው የሚል መፈክር ባንዱ ካድሬአቸው ከተፈጠረ በኌላ መንጌ አንድ አይን ጠፉ :: ከዛን ጊዜ በኌላ ገበሬዎች ጋ ሄደው ዘንድሮ ምን ማምረት እንዳለባቸው መመሪያ ከሰጡ በሚቀጥለው የምርት ዘመን እሳቸው የጠቀሱት የእህል አይነት የአገሪቱን ጎተራ ይሞላል …ጂኦሎጂስቶችን ምን አይነት Mineral (ore) ማውጣት አንዳለባቸው ከነገሩአቸው ርብርቡ ሁሉ እዛ ላይ ይሆናል :: አንድ ሰሞንማ ለዶክተሮች እንዴት ማከም እንዳለባቸው ዎርክሾፕ ሰጥተው ነበር ይባላል . ያ ነው እንግዲህ “ኢንዲሚክ ወፍ የተባለላቸው መንጌን እንደ ወፍ ካገር በረው እንዲጠፉ ያደረጋቸው :: እና እውነቱን እንነጋገር ከተባለ ይሄ ጥፋት የመንጌ ብቻ አይደለም … በዙሪያቸው ያሉ ስብስቦች ለምንጌ ” ሱፐርይርርና አሮጋንት ፐርሰናሊቲ “መፈጠር መዋጮ አድረገዋል :: ሰው ናቱራል ( Natural ) ከሆነው እሱነቱ ወጥቶ ሰው ሰራሽ ሰው ሲሆን ራሱም ችግር ላይ ወድቆ ለሌላውም ችግር ይሆናል :: በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ሳጥናኤል መልከ -መልካም እንደነበር እንደውም ሉሲፈር የሚባል ስም እንዳለው ና ከእግዛብሄር ዋና መላክቶች ሚካኤልና ገብሬል በላይም እንደነበር የእጊዚአብሄር ቃል ያስተምራል :: እንዳልኩት ሉሲፈር ቆንጆ ነበር :: አካባቢውን ዞር ዞር ብሎ ሲያይ በሱ አምሳል የተፈጠሩት በሙሉ እንደሱ ውብ መስለው አልታይህ አሉት :: እናም በልቡ ውስጥ ትእቢት ተጸነሰ :: ታዲያ የዚህ ትእቢት መጨረሻው ከ 7ኛው ሰማይ ወደ ምድር መወረውር ሆነ :: ይሀው እሱ ምድር ላይ በመሆኑ እኛም ሁላችን መከራ እናያለን :: እሱም የዚህ ትልቅ ውቅያኖስ አካል ነውና :: ትእቢት መጥፎ ነው ለማንም አልበጀ ..ለሉሲፈርም አልሆነው ..የትእቢት ትንሽም የለውም :: ሳምቡሳ ወይም ቦርዴ ጠላ የፈጠረውም ትእቢትም ሆነ የሉስፈርም ትእቢት መጨረሻቸው ወይም መድረሻቸው አንድ ነው …… እንጦርጦስ :: ታዛቢው ነኝ..

Show Buttons
Hide Buttons