” 400 ሺህ ብር ክፈል ይሉኛል። እኔ ይሄን ያህል ገንዘብ ከየትም ላመጣ አልችልም። … ልመና ወጥቻለሁ። ” – አባት…..

ኤርትራዊው ስደተኛ ባልታወቁ ሰዎች ተወስዶ ለማስለቀቂያ 400 ሺህ ብር እንደተጠየቀበት ተነገረ።

አባት ገንዘቡን ለማግኘት ልመና ወጥተዋል።

በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ በጭላ ቀበሌ በተቋቋመው የዓለምዋጭ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የሚኖሩት ኤርትራዊው ስደተኛ አቶ መሀመድ ኡስማን ባለፈው መጋቢት 26 ቀን 2016 ልጃቸው አማን መሀመድ መታገቱን ገልጸዋል።

ልጃቸው በአቅራቢያ ካለው የዳባት ትምህርት ቤት ቀን 10:00 እየተመለሰ እያለ ባልታወቁ ሰዎች መታገቱን አመልክተዋል።

አጋቾቹ በየሁለት ቀን በመደወል የማስለቀቂያ ገንዘብ እየጠየቋቸው እንደሆነ ጠቁመዋል።

አባት አቶ መሀመድ ፥ ” እየደወሉ 400 ሺህ ብር ክፈል ብለውኛል። እኔ ይሄን ያህል ገንዘብ ከየትም ላመጣ አልችልም። እስከዚህች እለት ድረስ ይኸው በየአብያተክርስቲያናቱ እና በየመስጂዱ ለልጄ ማስለቀቂያ የሚሆን ገንዘብ ለማሰባሰብ ልመና ላይ ነኝ። ሌሎች ስደተኞችም በልመና ይተባበሩኛል እስካሁን የተገኘ ገንዘብ የለም ” ብለዋል።

አጋቾቹ በየደወሉ ቁጥር ልጃቸው እያለቀሰ ድምፁን እንደሚያሰሟቸውም ገልጸዋል።

ልጃቸው በተለምዶ ” ባጃጅ ” በሚባለው ባለ3 እግር ተሽከርካሪ ታግቶ መወሰዱን ገልጸው የሰሌዳ ቁጥሩን ለፖሊስ ቢያመለክቱም እስካሁን ውጤት የለም።

የኢትዮጵያ የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት ፥ ” አንድ ልጅ የጠፋ አለ እገታ ሳይሆን አይቀርም የሚል መረጃ ስለመጣ እንደተቋም ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን የማጣራት ስራ እየሰራን ነው ” ብሏል።

የጭላ ቀበሌ አስተዳዳሪ አቶ ምናለ ግንብነህ በበኩላቸው ፥ ከህፃኑ ጋር ሌላ የአስተማሪ ልጅም መወሰዱን ጠቁመዋል።

” እንዴት ሄደ ? ወደየት ሄደ ? የሚለውን ፖሊስ እየሰራበት ነው ” ያሉት አስታዳዳሪው ” አንድ የታሰረ ልጅ አለ መረጃ ስጥ እየተባለ ነው ያለው ” ብለዋል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ ፡-(@tikvahethiopia)