የአፍሪካ ዋንጫ፡ አይቮሪ ኮስት እና ናይጄሪያ ለፍጻሜ አለፉ

ትናንት ምሽት በተደረጉት ሁለት የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች የውድድሩ አዘጋጅ ሀገር አይቮሪ ኮስት እንዲሁም ናይጄሪያ ለፍጻሜ መድረሳቸውን አረጋግጠዋል።

ቀደም ብሎ የተካሄደው የናይጄሪያ እና የደቡብ አፍሪካ ጨዋታ ሲሆን ‘ሱፐር ኤግሎች’ ባፋና ባፋናዎችን ከተጨማሪ ሰዓት በኋላ በተደረገ የመለያ ምት 4 ለ 2 በሆነ ውጤት ረተዋቸዋል።

የናይጄሪያው አጥቂ ኬሊቺ ኢንሄንቾ የመጨረሻውን የማሸነፊያ ምት በማስቆጠር ሀገሩን ለፍጻሜ አብቅቷል።

የናይጄሪያ እና የደቡብ አፍሪካ ጨዋታ ወደ መለያ ምት ከማምራቱ በፊት ቡድኖቹ 1 ለ 1 በሆነ ውጤት መደበኛውን እና ተጨማሪውን ሰዓት አጠናቀዋል።

በ 64ኛው ደቂቃ አጥቂው ቪክተር ኦሰሜን በተሰራ ጥፋት ምክንያት ለናይጄሪያ ፍጹም ቅጣት ምት ተሰጥቷል። የናይጄሪያ ብሄራዊ ቡድን አምበል ዊሊያም ትሩስ ኢኩንግ በ67ኛው ደቂቃ ላይ ፍጽም ቅጣት ምቱን አሰቆጥሮ ናይጄሪያ እንድትመራ አድርጓል።

84ኛው ደቂቃ ናይጄሪያ በቪክተር ኦሰሜን አማካኝነት ሁለተኛ ጎል አስቆጥራ የነበረ ቢሆንም በቪዲዮ የታገዙት ዳኛው የናይጄሪያን ግብ ሽረው ለደቡብ አፍሪካ ፍጹም ቅጣት ምት ሰጥተዋል።

ለግቡ መነሻ የነበረው ኳስ በናይጄሪያ የግብ ክልል ውስጥ የተሰራ ጥፋትን አልፎ ስለነበር በዳኛው የተሰጠውን ፍጹም ቅጣት ምት ደቡብ አፍሪካዎች አስቆጥረው ወደ ተጨማሪ ሰዓት እና መለያ ምት የሄደበትን ጎል ቴቦሆ ሞኮና አስቆጥሯል።

በተጨማሪው ሰዓት የደቡብ አፍሪካው ተከላካይ ግራንት ኬካና በሰራው ጥፋት በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል።

ምሽት አምስት ሰዓት በተካሄደው ሌላኛው ጨዋታ ደግሞ ሰባስቲያን ሃለር በስቆጠራት ብቸኛ ጎል አዘጋጇ ሀገር አይቮሪ ኮስት ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎን በመርታት ለዋንጫ ደርሳለች።

በአቢጃን በተካሄደው ጨዋታ አይቮሪ ኮስትን አሸናፊ ያደርጋት ብቸኛ ጎል በ65ኛው ደቂቃ የተቆጠረ ነው።

ጨዋታው ቀጥሎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎዎች ሙከራዎችን ቢያደርጉም አቻ ወይም አሸናፊ የሚያደርጋቸውን ጎሎች ማስቆጠር አልቻሉም።

አይቮሪ ኮስት በምድብ ጨዋታዎች በነበራት ደካማ አቋም ምክንያት አሰልጣኟን ዤን ሎይስ አሰናብታ ነበር። የመጨረሻውን የምድብ ጨዋታ በደጋፊዎቿ ፊት 4 ለምንም የተረታች ሲሆን ምርጥ ሶስተኛ ሆና ወደ ጥሎ ማለፍ ተሸጋግራለች።

ቀጥሎ ባለው ጨዋታ የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮኗን ሴኔጋል፣ ማሊን እንዲሁም ትናንት ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎን ረታ ለፍጻሜው መድረስ ችላለች።

የፍጻሜው ጨዋታ ዕሁድ ማታ አምስት ሰዓት የሚከናወን ይሆናል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዝዝ ብቻ ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤ ለተጨማሪ መረጃ ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/
ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazonnnn

ምንጭ (ቢቢሲ)