” የቲክቶክን አደጋ በትክክል እናውቃለን ” – ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን

‘ ቲክቶክ ‘ አውሮፓ ውስጥ የመታገድ ዕጣፋንታ ሊገጥመው እንደሚችል ተሰማ።

ባለፈው ሳምንት አሜሪካ ‘ ቶክቶክ ‘ በመላ ሀገሪቱ እንዲታገድ አልያም ለአሜሪካ ኩባንያ እንዲሸጥ ሕግ ማውጣቷ ይታወቃል። ለዚህም የሰጠችው ጊዜ ከ9 ወር እስከ 1 ዓመት ብቻ ነው።

አሁን ደግሞ መተግበሪያው የአውሮፓ ሀገራት ውስጥ የመታገድ ዕጣፋንታ ሊገጥመው እንደሚችል ተነግሯል።

የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን ለኮሚሽኑ የ2024 ምርጫ በተደረገ አንድ ክርክር ላይ ‘ ቲክቶክ ‘ በአውሮፓ ሀገራት የመታገድ ዕጣፋንታው ዝግ እንዳልሆነ ጠቁመዋል።

ይህን ያሉት የአሜሪካ ‘ ቲክቶክ ‘ ን የማገድ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ መድረሷን በተመለከተ ለተነሳላቸው ጥያቄ ነው።

ቮን ደር ሌየን ኮሚሽኑ ከመላው ዓለም በተቋሙ ስልኮች ላይ መተግበሪያው እንዳይሰራ ያደረገ የመጀመሪያ ተቋም መሆኑን አስታውሰዋል።

” የቲክቶክን አደጋ በትክክል ምንእንደሆነ እናውቃለን ” ሲሉ አክለዋል።

ምንም እንኳን የአውሮፓ ኮሚሽን አውሮፓ ሀገራት ውስጥ ‘ ቲክቶክ ‘ ሊታገድ እንደሚችል ፍንጭ ቢሰጥም ልክ እንደ አሜሪካ በፍጥነት ተመሳሳይ መንገድ ይከተል እንደሆነ ለመደምደም ገና ነው ተብሏል።

የአውሮፓ ኮሚሽን በቅርቡ ከዋናው ቲክቶክ አነስ ብሎ የተዘጋጀው ‘ ቲክቶክ ላይት (ተጠቃሚዎች ተከፍሏቸው ቪድዮ የሚያዩበት) ‘ በህጻናት እና ተጠቃሚዎች የአዕምሮ ጤንነት ላይ ሊያስከትል ስለሚችለው አደጋ ጥያቄ ማንሳቱ ይታወሳል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ(@tikvahethiopia)