” የሟች ቤተሰብ ተገኝቷል ” – ፖሊስ

በሟች ኪስ ማንነቱ የሚጠቅስ መረጃ በማጣቱ  ምክንያት የሟችን ፎቶ በመለጠፍ  ቤተሰቦቹን አፋልጉኝ ያለው የዓዲግራት ከተማ ፓሊስ የሟች ቤተሰብ መገኘቱ አስታውቋል።

የማህበራዊ የትስስር ገፆችና ሚድያዎች በሟች ቤተሰብ ፍለጋ ያደረጉት የነቃ ወገናዊ ተሳትፎና ጥረት አመስግኗል።

ለሟቹ ቤተሰብ ክብር ሲባል ፎቶውን ከገፃቸው በማጥፋት እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርቧል።

በዚህም መሰረት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለሟች ቤተሰብ ክብር የሟችን ፎቶ #ማጥፋቱን ለመላ አባላቱ መግለጽ ይወዳል።

ምናልባት በውስጥ የተቀባበላችሁም የሟችን ፎቶ ከስልካችሁ እንድታጠፉ እንጠይቃለን።

ሚያዝያ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት በዓዲግራት ከተማ አንድ ወጣት ተገድሎ ተጥሎ መገኘቱንና በግድያው የተጠረጠሩ 3 ግለሰቦች ሟቹ ከወደቀበት አቅራቢያ በሚገኝ አንድ መጠጥ ቤት በቁጥጥር ስር መዋላቸው መረጃ እንደላክልንላችሁ ይታወሳል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ ፡-(@tikvahethiopia)