ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ተደረጉ…..

የዓድዋ መታሰቢያ ሙዚየም የካቲት 03 ቀን 2016 ዓ.ም ይመረቃል።

የምረቃ ስነ-ስርዓትን ተከትሎ በዕለቱ ከቀኑ 6 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ተደርገዋል፡፡

በዚህም መሰረት:-

➡ ከአፍንጮ በር ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን፣

➡ ከሰሜን ሆቴል ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን፣ከዮሃንስ ቤተ ክርስቲያን ወደ አቡነ ጴጥሮስ፣

➡ ከአራት መንታ ወደ ጅንአድ፣

➡ ከይርጋ ሃይሌ የገበያ ማዕከል ወደ አቡነ ጴጥሮስ፣

➡ ከሃብተ ጊዮርጊስ ድልድይ ወደ ሱማሌ ተራ ፣

➡ከሱማሌ ተራ ወደ ኤሊያና ሆቴል(ባንኮዲሮማ) መስቀለኛ፣

➡ ከተክለ ሃይማኖት አደባባይ ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ

➡️ ከሀገር አስተዳደር መብራት (ኢሚግሬሽን) ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ፣

➡️ ከንግድ ማተሚያ ቤት ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ፣

➡️ ከአሮጌው ቄራ ወደ ባንኮ ዲሮማ መብራት፣

➡️ ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ደጎል አደባባይ፣

➡️ ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ፣

➡️ ከመቅደላ ሆቴል ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን፣

➡️ ከቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ወደ ቴሌ እና ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት ወደሚገኘው አደባባይ የሚወስዱት መንገዶች በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት (የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 6 ሰዓት ጀምሮ) ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

አሽከርካሪዎች ይህንን ተገንዝበው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ እና የትራፊክ ፖሊሶች በሚጠቁሟቸውን አማራጭ አቅጣጫዎችን በመጠቀም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

በዋዜማው የካቲት 2 ቀን 2016 ዓ.ም ከላይ በተጠቀሱት መንገዶችና የምረቃ ስነ-ስርዓቱ በሚከናወንበት በዓድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ዙሪያ ተሽከርካሪ ማሳደርም ሆነ ለአጭርም ሆነ ለረጀም ሰዓት አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑንም ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ይለፍ ያላቸው አሽከርካሪዎች ቸርችር ጎዳና ጫፍ የቀድሞ ሜክሲኮ ታክሲ ተራ እና ከቴዎድሮስ አደባባይ እስከ ቸርችር ጎዳና ጫፍ መኪናዎቻቸውን መቆም ይችላሉ።

ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ እንደሚኖር በመገንዘብ ታዳሚዎች የተለመደ ትብብር እንዲያደርጉ መልዕክት ተላልፏል።

የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ጥሪ ከተደረገላቸው እንግዶች ውጪ ወደ ሙዚየም የሚወስዱ መንገዶች ዝግጅቱ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለእግረኞች ዝግ ይሆናሉ።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ ፡-@tikvahethiopia