ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች ጋር በቢሯቸው መምከር መጀመራቸው ተነግሯል….

ዶ/ር ዐቢይ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የነበሩትን ስራዎች እና መሻሻሎች ላይ ነው ግምገማ ማካሄድ የጀመሩት።

በዚህ የግምገማ መድረክ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች በተጨማሪ የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናትም ተገኝተዋል።

የጠቅላይ ሚ/ር ፅ/ቤት ” ይህ በፌደራል እና የክልል ኃላፊነት ባላቸው የስራ ተዋንያን የሚደረገው ጠቃሚ ግምገማ በድኅረ ግጭት መልሶ ግንባታ እና በሰላም ስምምነት አፈጻጸም ላይ ያተኮረ ነው። ” ብሏል።

በዛሬው መድረክ የህወሓት ሊቀመንበር እና የቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዜዳንት ዶክተር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በአካል ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ተገናኝተዋል፡፡

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ ፡-@tikvahethiopia