ዓመታዊው የቁልቢ ገብርኤል ንግስ በዓልን ተከትሎ፤ከታህሳስ 17 እስከ ታህሳስ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ከሰዓት ባሉት ቀናት ከጨለንቆ እስከ ቀርሳ ባሉት ከተሞች ዋና መንገድ ላይ ከባድ ተሽከርካሪ ማለፍ ክልክል ነው

ታህሳስ 19 የሚከበረው ዓመታዊው የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በዓል ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን ጊዚያዊ የፀጥታ ግብረ ኃይል አሳውቀዋል።

ለበዓሉ የሚያቀኑ አሽከርካሪዎች አካባቢው ዳገት፣ ቁልቁለት እና ጠመዝማዛ መንገድ ስለሚበዛው ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የትራፊክ ህግና ደንብ አክብረው እንዲያሽከረክሩ ማሳሰቢያ ተለልፏል።

ከታህሳስ 17 እስከ ታህሳስ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ከሰዓት ባሉት ቀናት ከጨለንቆ እስከ ቀርሳ ባሉት ከተሞች ዋና መንገድ ላይ ከባድ ተሽከርካሪ ማለፍ ክልክል መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪ ፦

– የጸጥታ አካላት ቋሚና ተንቀሳቃሽ ጥበቃ እያደረጉ ይገኛሉ።

– በበዓሉ ወቅት ተጠርጣሪ ወንጀለኞች ሲያዙ ፈጣን ውሳኔ ለመስጠት እንዲቻል ጊዜያዊ ፍርድ ቤት በአቅራቢያ ተቋቁሟል።

– ጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያዎች ተቋቁሟል።

የበዓሉ ታዳሚዎች ንብረቶቻቸውን #በጥንቃቄ እንዲይዙ መልዕክት ተላልፏል። ማንኛውም አጠራጣሪ ጉዳይ ካጋጠመ በአቅራቢያ ላለ የፀጥታ አካል ጥቆማ መስጠት ይቻላል።

በተመሳሳይ ፤ በሀዋሳ ለሚከበረው የቅዱስ ገብርዔል ዓመታዊ የንግስ በዓልን አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉ ተነግሯል።

ለበዓሉ የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል ብሎም ደህንነታቸው ተጠብቆ በከተማዋ ውስጥ መንቀሳቀስ እንዲችሉ ሁሉም አካል በትብብር እየሰራ ነው ተብሏል።

ስርቆት፣ ያለአግባብ ዋጋ ጭማሪ ፣ ማጭበርበር እንዳይፈፀም የጥንቃቄ ስራ እየተሰራ መሆኑን የከተማ አስተዳደር አሳውቋል።

በዓሉ በሚከበርበት ዕለትና ሥፍራ ወንጀል ተፈፅሞ ቢገኝ አፋጣኝ ፍትህ የሚሰጥ ጊዜያዊ ችሎት መሰየሙ ይፋ ተደርጓል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዝዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazonnnn

(ምንጭ)tikvahethiopia