ከአንድ ሳምንት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ሚሊኒያም አዳራሽ አካባቢ ከፖሊስ ኃይል ጋር በነበረው የተኩስ ልውውጥ ወቅት ሁለት ” የፋኖ አባላት (አንድ አመራር እና አንድ አባል) ” መገደላቸው መነገሩ ይታወሳል።

– ናሁሰናይ አንዳርጌ

– አቤነዘር ጋሻው መገደላቸው መነገሩ ይታወሳል።

ከዛ በኃላ እናቶቻቸው በሀዘን ውስጥ ሆነው አስክሬን ለመውሰድ እንዳልቻሉና እላይ ታች እያሉ እንደሆነ ግን ምንም መፍትሄ እንዳላሀኙ ተነግሮ ነበር።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ትላንት ምሽት ለቪኦኤ ቃላቸውን የሰጡ አንድ የቤተሰቡ አባል ፥ እስካሁን አስክሬን ለቤተሰብ እንዳልተጠ ተናግረዋል።

የናሁሰናይ አንዳርጌ እናት ወ/ሮ ሀረገወይን አዱኛ እና የአቤነዘር ጋሻው እናት ወ/ሮ ኤልሳ ሰለሞን የልጆቻቸውን አስክሬን ለመጠየቅ በየቦተው እየተንከራተቱ እንደሆነ ገልጸዋል።

” እንድህ ያለው ክስተት በዓለም ላይ ያልተከሰተ እስኪመስል ድረስ ነው ከሀዘን በላይ ስቃይ ሆኗል። በጥዋት ጉዳይ አስፈጻሚ መስለው ነው የሁለቱ እናቶች የሚሄዱት አዲስ አበባ ፖሊስ ይሄዳሉ ‘ እኛን አይመለከትም ፌዴራል ነው ‘ ይባላሉ ፌዴራል ይሄዳሉ ‘ እኛን አይመለከትም ‘ ይባላሉ ከዛ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ እዛ ጭራሽ የሚያናግራቸው የለም ” ብለዋል።

” ማንም ሰብዓዊ ሰው ይሄን ይረዳል ብዬ አስባለሁ። ሰው ሞቶ አስክሬን የተከለከልን ብቸኛ ሰዎች እኛ ነን ብዬ ነው የማስበው አስክሬን ማየት እንኳን ተከልክለናል። ” ሲሉ አክለዋል።

ከቀናት በፊት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ይሄ ጉዳይ የሚመለከተው የፀጥታ እና ደኅንነት ግብረ ኃይል ወይም የፌደራል ፖሊስን እንደሆነ መናገሩ ይታወሳል።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ደግሞ ፥ ” ይህ ጉዳይ የሚመለከተው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ነው ” ማለቱ አይዘነጋም።

በሌላ በኩል ፥ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ አስክሬን ለመጠየቅ የሄዱ ሁለት የቤተሰብ አባላት (ዳዊት መንግሥቱ እና ዳዊት መኮንን የተባሉ) መታሰራቸውን እኚሁ የቤተሰብ አባል ገልጸዋል።

” መንግሥት ከሚለው አይነት ነገር ጋር ምንም ግንኝኑት የላቸውም በግል ስራ ነው የሚተዳደሩት አክሬን ለመጠየቅ ሲሄዱ ነው ቤታቸው እንዲፈተሽ ተደርጎ በቁጥጥር ስር የዋሉት ” ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው አስረድተዋል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ ፡-(@tikvahethiopia)