አርሰናል ከ ሊቨርፑል፡ ለዋንጫ ፉክክሩ ብዙ ትርጉም የሚሰጠውን ጨዋታ ማን ያሸንፋል?

አርሰናል ከሊጉ መሪ ሊቨርፑል አምስት ነጥቦችን ርቆ ይገኛል። መድፈኞቹ ትክክለኛ የዋንጫ ተፎካካሪ ሆነው መቅረባቸውን የሚያረጋግጡት እንደነዚህ ዓይነት ጨዋታዎችን በማሸነፍ ነው ይላል የቢቢሲው እግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱቶን።

አርሰናል ማሸነፍ አለበት። ይህን ጨዋታ ሊቨርፑል የሚያሸንፍ ከሆነ አርሰናል ሊቨርፑል ላይ በነጥብ መድረስ አይደለም አይጠጋውም።

የሳምንቱ ማብቂያ የፕሪሚየር ሊግ እግር ኳሰስ ግጥሚያዎችን በተመለከተ የሱቶን ግምቶች እንደሚከተለው ቀርበዋል።

ኤቨርተን ከ ቶተነሃም

ይህን ጨዋታ ያለፉትን አምስት ጨዋታዎች ማሸነፍ ላቃቸው ኤቨርተኖች በጣም ከባድ ነው። በስድስት ጨዋታዎች ሁለት ግቦችን ብቻ ማስቆጠር የቻሉት ኤቨርተኖች ወደ ወራጅ ቀጠና ተንሸራተዋል።

ቶተነሃም አምበሉን ቢያጣም በዚህ ጨዋታ እንደማይሸነፍ እገምታለሁ። ቶተነሃም በመልሶ ማጥቃት ኤርተንን ይፈትናል።

ግምት፡ ኤቨርተን 2 – 2 ቶተነሃም

ብራይተን ከ ክርስታል ፓላስ

አሁን ላይ ስለ ብራይተን ምን ማለት እንኳ እንዳለብኝ አላውቅም። በዚህ ሳምንት አጋማሽ በሉተን የገጠማቸው ጨርሶ የጠበቁት አልነበረም።

ያሸንፋል ተብሎ ተገምቶ በሰፊ የግብ ልዩነት መሸነፍ አይጠበቅም።

ፓላስ ደግሞ በኤዜ እና ማይክል ኦሊሴ አስደናቂ ጥምረት ግብ እያገኘ ነው።

ምንም እንኳ በብራይተን ባልተማመንም ይህን ጨዋታ ብራይተን የሚያሸንፍ ይመስለኛል።

ግምት፡ ብራይተን 2 – 1 ክርስታል ፓላስ

በርንሊ ከ ፉልሃም

በጣም በተደጋጋሚ በርንሊ ማሸነፍ ግድ ይለዋል ስል ቆይቻለሁ ነገር ግን ይህን ማድረግ ተስኖት ቆይቷል። ይህን ጨዋታም በሜዳው እንደማድረጉ ማሸነፍ ግድ የሚለው ቢሆንም ጨዋታው በአቻ የሚጠናቀቅ ይመስለኛል።

ይህን እንድል ያስገደደኝ ደግሞ ፉልሃም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግብ ማስቆጠር ስለተሳነው ነው። ምናልባት አዲሱ ፈራሚያቸው አርማንዶ ብሮያ መፍትሄ ይሰጣቸው ይሆናል።

ግምት፡ በርንሊ 1 – 1 ፉልሃም

ኒውካስል ከ ሉተን

ሁለቱም ቡድኖች በሳምንቱ አጋማሽ አስደናቂ ውጤቶችን አስመዝግበዋል። በአሁኑ ወቅት የሁለቱም ክለቦች ተነሳሽነት ከፍ ያለ ነው።

ግን ከቡድን ጥራት እንዲሁም ኒውካስል በሜዳው አስፈሪ መሆኑን ከግምት በማስገባት፤ ይህን ጨዋታ ባለሜዳዎቹ እንደሚረቱ አስባለሁ።

ግምት፡ ኒውካስል 3 – 1 ሉተን

ሼፊልድ ዩናይትድ ከ አስተን ቪላ

ከጥቂት ሳምንታት በፊት ሼፊልድ አስተን ቪላን ነጥብ አስጥሎ ነበር። አሁን ግን ቪላ ይህ እንዲሆን የሚፈቅድ አይመስለኝም።

የኡናይ ኤምሪ ቡድን ይህን ጨዋታ የማያሸንፍ ከሆነ ገንብቶት የነበረውን መልካም ስም የሚያጣ ይመስለኛል።

ግምት፡ ሼፊልድ 1 – 2 አስተን ቪላ

ቦርንመዝ ከ ኖቲንግሃም ፎረስት

ይህ ጨዋታ ለፎረስት በጣም ወሳኝ ነው።

ሁለቱ ክለቦች ከጥቂት ሳምንታት በፊት በተገናኙበት ወቅት ቦርንመዝ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ባስቆጠረው ግብ የኑኖ ኢስፒሪቶ ሳንቶስ ቡድንን ማሸነፍ ችሎ ነበር።

የቦርንመዝ አጥቂ ዶሚኒክ ሶላንኬ ካለበት አስደናቂ አቋም አንጻር ይህን ጨዋታ ባለሜዳዎቹ እንደሚያሸንፉ እገምታለሁ።

ግምት፡ ቦርንመዝ 2 – 1 ፎረስት

ቼልሲ ከ ዎልቭስ

ቼልሲ ከሽነፈቱ ለማገገም ይህን ጨዋታ ማሸነፍ ይኖርበታል። ቼልሲ ከሊቨርፑል ጋር ሲጫወት በጣም ደካማ ሆኖ ታይቷል።

ቼልሲ ለተጫዋቾች ዝውውር ወጪ ካደረገው ከፍተኛ ገንዘብ አንጻር እያሳየ ያለው አቋም እጅግ ደካማ ነው።

ፖቸቲኖ ለውጥ ማምጣት አለባቸው። ከዚህ ጨዋታ ሙሉ ነጥብ የሚያገኙ ግን አይመስለኛም። ይህን የምለው ከምመለከተው አንጻር ነው።

ዎልቭስ የተደራጀ እና በመልሶ ማጥቃት አደጋ የሚፈጥር ቡድን ነው። ይህ ጨዋታ በአቻ ውጤት ይጠናቀቃል።

ግምት፡ ቼልሲ 1 – 1 ዎልቭስ

ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ዌስት ሃም

ዩናይትድ በሞለኒዩ ጥሩ ተጫውቶ የሚገባውን ነጥብ አግኝቷል።

ከገና በፊት ዩናይትድ ወደ ዌስት ሃም ሜዳ ተጉዞ ሽንፈት ተከናንቦ መመለሱ አይዘነጋም። በዚህ ጨዋታ ደግሞ ዩናይትድ በተራው የሚያሸንፍ ይመስለኛል።

ግምት፡ ዩናይትድ 1 – 0 ዌስት ሃም

አርሰናል ከ ሊቨርፑል

አሁናዊው የሊቨርፑል አቋም በጣም ጥሩ ነው። ከቼልሲ ጋር በነበራቸው ጨዋታ በጣም አስናቂ ነበሩ። ሞ ሳላህ ደግሞ ከአፍሪካ ዋንጫ ተመልሷል። ተሰልፎ ሊጫወትም ይችላል።

የትሬንት አሌክሳንደር-አርኖልድ እና አንዲ ሮበርትሰን ከጉዳት መመለስም ለሊቨርፑል መልካም ዜና ነው። ከዚህ በተጨማሪ አጥቂው ኑኔዝ የሚያገኛቸውን አጋጣሚዎች ወደ ጎል እየቀየረ ይገኛል።

በሌላ በኩል አርሰናል ፎረስትን እንዲሁ በቀላሉ አልነበረም የረታው።

የማይክል አርቴታ ቡድን በዚህ ጨዋታ የሚያገኘውን ዕድል የሚጠቀም ከሆነ ሙሉ ነጥብ ሊያገኝ ይችላል።

ሊቨርፑል በዚህ ጨዋታ ግብ ያስቆጥራል። ጨዋታውን ግን አርሰናል እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ። የማይካደው ነገር ይህ ጨዋታ የዋንጫ ፉክክሩን ወዴት ሊያመራ እንደሚችል ጠቋሚ እንደሆነ ሁሉም የሚስማማበት ነው።

ግምት፡ አርሰናል 2 – 1 ሊቨርፑል

ብሬንትፈርድ ከ ማን ሲቲ

ባለፈው የውድድር ዓመት ብሬንትፈርድ ባልተጠበቀ ሁኔታ አንዴ ብቻ ሳይሆን ሁለት ጊዜ ሲቲን ማሸንፍ ችሎ ነበር። ንቦቹ ይህን ስኬታቸውን አሁንም ይደግሙታል ብዬ ግን አላስብም።

በዚህ ጨዋታ ብሬንትፈርድ ግብ ማስቆጠሩ አይቀርም። ሲቲ ግን ብዙ ያገባል።

ግምት፡ ብሬንትፈርድ 1 – 3 ሲቲ

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዝዝ ብቻ ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤ ለተጨማሪ መረጃ ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/
ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazonnn

ምንጭ ( ቢቢሲ )