ናይጄሪያ እና ዴሞክራቲክ ኮንጎ ተጋጣሚዎቻቸውን አሽንፈው ግማሸፍ ፍጻሜውን ተቀላቀሉ

በአይቮሪ ኮስት አዘጋጅነት እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ዋንጫ ናይጄሪያ እና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ተጋጣሚዎቻቸውን በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀሉ።

ትናንት አርብ ምሽት ቀድሞ የተካሄደው ጨዋታ ናይጄሪያ እና አንጎላን ያገናኘው ነበር።

በመጀመሪያው አጋማሽ ከዚህ ቀደም ለእንግሊዝ ከ21 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ይጫወት የነበረው አዴሞላ ሉክማን ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ ናይጄሪያ ለግማሽ ፍጻሜ መድረሷን ያረጋገጠች ሆናለች።

ለናይጄሪያ አሸናፊነት በቂ የሆነችው የሉክማን ግብ በሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ያስመገባት ሦስተኛ ግቡ ሆናለች።

የግብ ማስቆጠር አጋጣሚዎችን አግኝተው የነበሩት አንጎላዎች አደገኛ ሙከራዎችን ቢያደርጉም ኳስ ከናይጄሪያው ግብ ጠባቂ ማለፍ አልቻለችም።

ናይጄሪያ በቀጣይ ከኬፕ ቨርድ እና ደቡብ አፍሪካ አሸናፊን የምትገጥም ይሆናል።

በሁለተኛው ጨዋታ ዴሞክራቲክ ኮንጎ ከመመራት ተነስታ ጊኒን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችላለች።

በ20ኛ ደቂቃው ጊኒ ብዙዎችን ያለሳመነ ፍጹም ቅጣት ምት ካገኘች በኋላ ሞሐመድ ባዮ ቡድኑን ቀዳሚ አድርጓል።

የፍጹም ቅጣት ምት ሳጥን ውስጥ ኳስ በእጅ ነክቷል ተብሎ ቡድኑ ላይ ፍጹም ቅጣት ምት ያሰጠው ተከላካዩ ቻንሰል ምቤማ ብዙ ሳይቆይ ግብ አስቆጥሮ ኮንጎን አቻ ማድረግ ችሏል።

በሁለተኛው አጋማሽ በተመሳሳይ ዴሞክራቲክ ኮንጎ ፍጹም ቅጣት ምት አግኝታ የብሬንትፎዱ የፊት መስመር ተጫዋች ዕድሉን ወደ ግብ ቀይሯል።

አርተር ማሱዋኩ በቅጣት ምት ያስቆጠራት 3ኛዋ ግብ በሁለት ጎል ልዩነት የኮንጎ አሸናፊነትን ያረጋገጠች ሆናለች።

ዴሞክራቲክ ኮንጎ በዚህ ውድድር ያደረገቻቸው አራት ጨዋታዎችን በሙሉ በአቻ ውጤት አጠናቃ ነው ወደ ጥሎ ማለፉ የገባቸው። በጥሎ ማለፉ ዙር ደግሞ ግብፅን በፍጹም ቅጣት ማሸነፏ ይታወሳል።

ኮንጎ በግማሽ ፍጻሜው ከማሊ እና አይቮሪ ኮስት አሸናፊ ጋር የምትገናኝ ይሆናል።

ቀሪዎቹ ሁለት የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ዛሬ ቅዳሜ ጥር 25/2016 ዓ.ም. ምሽት 2 ሰዓት እና 5 ሲል ይካሄደሉ።

የመጀመሪያው ግጥሚያ ማሊን ከአዘጋጇ አይቮሪ ኮስት የሚያገናኝ ሲሆን፣ ቀጥሎ የሚደረገው ግጥሚያ ደግሞ ኬፕ ቨርድ እና ደቡብ አፍሪካ የሚያደርጉት ነው።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዝዝ ብቻ ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤ ለተጨማሪ መረጃ ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/
ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazonnn

ምንጭ ( ቢቢሲ )