ባልታወቁ የታጠቁ ኃይሎች የመርቆ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ተቃጠለ……

 ” አልታወቁም ” በተባሉ የታጣቂ ኃይሎች በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ፤ በቦሰት ወረዳ ቤተ ክህነት የመርቆ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን መቃጠሉን የተዋሕዶ ሚዲያ አገልግሎት አሳውቋል።

” ባልታወቁ የታጠቁ ኃይሎች  ” ተፈፅሟል የተባለው ይህ የመቃጠል ተግባር ትናንት ጥር 17 ቀን 2016 ዓ.ም አመሻሽ ላይ መፈፀሙ ተመላክቷል።

” በቦታው ላይ የተለያዩ አካላት በተደጋጋሚ ጊዜ ዛቻና ማስፈራሪያ ሲያደርጉ ቆይቷል ” ያለው ዘገባው ትላንንት ሙሉ በሙሉ ንዋዬ ቅድሳቱ የተቃጠለ ሲሆን የቤተ መቅደሱ የውስጥና የውጭ ክፍል ጉዳት ያደረሰ ከፍተኛ ቃጠሎ መድረሱ ተገልጿል።

ጉዳዩ ላይ ሀገረ ስብከቱ አስፈላጊውን የማጣራት ሥራ እየሠራ ይገኛል ተብሏል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon