” በጎርፍ የተወሰዱ አስክሬኖች #አልተገኙም ” – የሀላባ ዞን ሰላምና ጸጥታ ጉዳይ መምሪያ!!!!!

ከሰሞኑን በሀላባ ዞን ንፋስ እና በረዶ ቀላቅሎ በጣለ ዝናብ በተከሰተ ከባድ የጎርፍ አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት ማለፉን መረጃ እንደሰጠናችሁ ይታወሳል።

በወቅቱ 5 ሰዎች መሞታቸዉንና ከነዚህ ዉስጥ የ2 ሰዎች አስከሬን አለመገኘቱ መግለጹ አይዘነጋም።

አስክሬን ፍለጋው ከምን ደረሰ ? ከአደጋው ጋር በተያያዘ ምን አዲስ ነገር አለ ? ስንል የሀላባ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ሀላፊን አቶ ሙደስር ጉታጎ ጠይቀናቸዋል።

ኃላፊው አስከሬኖቹ አሁን ድረስ አለመገኘታቸውን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ፤ አንድ አስክሬን በዞኑ መገኘቱን  በተደረገው ማጣራት አስከሬኑ ከስልጤ ዞን በጎርፍ ምክንያት የመጣ እንደሆነ ጠቁመዋል።

የጎርፍ አደጋው እስካሁን መሬት ላይ የነበረዉን ሰብል ሙሉ በሙሉ እንዳወደመ ገልጸዋል።

በዞኑ ውስጥ ባለው የሀላባ ቁሊቶ ሆስፒታል  ላይ ከ6 ሚሊየን 500 ሺህ ብር በላይ ጉዳት እንዳደረሰ ተናግረዋል። ነገር ግን ሆስፒታሉ አሁንም በስራ ላይ መሆኑን አመልክተዋል።

ከዚህ ቀደም የተገለጸው ዌራ ወረዳ ሆስፒታል ግን በአደጋው ምንም ሳይሆን ሙሉ በሙሉ ስራ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በአጠቃላይ ጎርፉ ያስከተለዉ አደጋ በህዝብና ግለሰቦች ላይ ከፍተኛ የሰብአዊ እና የንብረት ውድመት ያስከተለ ሲሆን ዞኑ አሁንም አስክሬን እና የጠፉ ሰዎችን የማፈላለጉ ስራ እንደቀጠለ መሆኑን ተናግረዋል።

አሁንም የአየር ትንበያ ዘገባዎች በደቡቡ ኢትዮጵያ ክፍል ከፍተኛ ዝናብ እንደሚኖር ስለሚጠቁሙ ማህበረሰቡ ሊከሰቱ ከሚችሉ አደጋዎች ራሱን እንዲጠብቅ መልዕክት ተላልፏል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ (@tikvahethiopia )