በመፈንቅለ-መንግሥት የተጠረጠሩት የቀድሞው የብራዚል ፕሬዝዳንት ቦልሶናሮ ፓስፖርታቸውን አስረከቡ

ምርመራ የተከፈተባቸው የቀድሞው የብራዚል ፕሬዝዳንት ጃይር ቦልሶናሮ ፓስፖርታቸውን አስረከቡ።

ባለፈው የአውሮፓውያኑ ዓመት ደጋፊዎቻቸው የብራዚልን ኮንግረስን ዘልቀው ገብተው አመፅ ከፈጠሩ በኋላ ነው ቦልሶናሮ ምርመራ የተከፈተባቸው።

ቦልሶናሮ በምርጫ በሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሳልቪ ከተሸነፉ በኋላ በግድ ሥልጣን ላይ ለመቆየት አቅደዋል ሲል ፖሊስ ይከሳቸዋል።

ቦልሶናሮ ይህ ፖለቲካዊ እርምጃ ነው እንጂ እኔ ይህን አላደርግኩም ሲሉ ያስተባብላሉ።

ሶስት የቦልሶናሮ ቀኝ እጅ የተባሉ ባልሥልጣናት በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

የፖለቲካ ፓርቲያቸው ፕሬዝዳንትም እንዲሁም በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ነው የሚገኙት።

ግለሰቦቹ ባለፈው ዓመት ጥቅምት ቦልሶናሮ በምርጫ ከተሸነፉ በኋላ ሥልጣን ላይ እንዲቆዩ አሲረዋል ተብለው ተከሰዋል።

የቦልሶናሮ ደጋፊዎች ምርጫው ተጭበርብሯል ብለው ያስባሉ። ፖሊስ ደግሞ ይህን ሐሳብ ያሰራጩት የቦልሶናሮ አጋሮች ናቸው ሲል ይከሳል።

ፖሊስ እንደሚለው ይህ ጉዳይ ነው ወደ መፈንቅለ-መንግሥት ሊቀይር ይችል ነበር።

ቦልሶናሮ ከጦር ሠራዊቱ ድጋፍ ሲያጡ የተበሳጩት ደጋፊዎቻቸው ባለፈው ዓመት ጥር የሀገሪቱን ኮንግረስ፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱን እና የፕሬዝዳንቱን መቀመጫ ወረዋል።

ይህ ሁሉ ሲሆን ቦልሶናሮ አሜሪካ ነበሩ።

ግርግሩን በማንሳሳት የተጠረጠሩት ቦልሶናሮ ባለፈው ሐሙስ ክሱን አስተባብለዋል።

“እኔ ሥልጣኔን ከለቀቅኩ አንድ ዓመት አልፎኛል ግን አሁን ማለቂያ የሌለው ክስ እየቀረበብኝ ነው” ሲሉ ለብራዚሉ ጋዜጣ ፎልሀ ተናግረዋል።

ፖሊስ ይህን ምርመራ አስመልክቶ የፕሬዝዳንቱን የተለያዩ ቤቶች ከፈተሸ በኋላ ነው ይህን ያሉት።

“እኔን እርሱኝ። አሁን ሀገሪቱን እየመራው ያለው ሌላ ሰው ነው” ሲሉ አክለዋል።

የቀድሞው መሪ ጠበቃ እንዳሉት ደንበኛቸው ሕጉን አክብረው ፓስፖርታቸውን ለፖሊስ ያስረክባሉ።

የቀድሞው ፕሬዝዳንት ደጋፊዎቻቸው ኮንግረሱን ከወረሩ ከሁለት ወራት በኋላ በአውሮፓውያኑ መጋቢት 2023 ነው ከሥልጣን የወረዱት።

ምንም እንኳ በርካታ ክሶች ቢቀርቡባቸውም እኔ የምፈራው ነገር የለም ይላሉ።

ባለፈው ሰኔ የብራዚል የምርጫ ሥነ-ሥርዓት ላይ ጥያቄ በመጫራቸው ምክንያት ለሚቀጥሉ ስምንት ዓመታት በምርጫ እንዳይወዳደሩ ታግደዋል።

ነገር ግን ደጋፊዎቻቸው የፈጠሩትን አመፅ ተከትሎ የተከፈተባቸው ዋነኛ ምርመራ የብዙዎችን ቀልብ ገዝቷል።

የብራዚል ፌዴራል ፖሊስ ሐሙስ ያደረገውን ምርመራ በተመለከተ ለጊዜው ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል። ነገር ግን “በመፈንቅለ መንግሥት ሙከራው የተሳተፉ የወንጀል ቡድኖችን” ዒላማ አድርገናል ብሏል።

ባለፈው ዓመት ብቻ 1400 ሰዎች በአመፁ በመሳተፋቸው በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሲሆን ፍርድ የተሰጣቸው ግን በጣም ጥቂቶች ናቸው።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዝዝ ብቻ ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤ ለተጨማሪ መረጃ ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazonnnn

ምንጭ (ቢቢሲ)