በሀሰተኛ የብር ኖት ግብይት የፈፀሙ 2 ተጠርጣሪዎች እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ጎሮ ገብርኤል አካባቢ መስከረም 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 12፡ 30 ሰዓት ላይ ነው።

ግለሰቦቹ ከአንድ ሸቀጣ ሸቀጥ መሸጫ እና ዘይት አከፋፋይ ከሆነ ሱቅ ውስጥ በርከት ያለ ባለ 20 ሊትር ዘይት ለመግዛት ተስማምተው ያስጭናሉ።

በኋላም ሒሳብ ሲከፍሉ ገንዘቡ ከባንክ እንደወጣና ህጋዊ ለማስመሰል አሽገው 42 ሺህ 350 ብር ለነጋዴው ይከፍሉታል፡፡

ሆኖም የግል ተበዳይ ገንዘቡ ሀሰተኛ መሆኑን ተጠራጥሮ በአካባቢ ነዋሪዎች ትብብር እንዲያዙ አድርጓል።

ተጠርጣሪዎቹ የግል ተበዳይ መጠራጠሩን ሲረዱ በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2 አ/አ 30791 ተሽከርካሪ በመጠቀም ለማምለጥ ቢሞክሩም በአካባቢው በነበሩ ሰዎች ሊያዙ ችለዋል።

ግብይት ሊፈፅሙበት ከነበረ 42 ሺህ 3 መቶ 50 ብር ውስጥ 39 ሺህ 4 መቶ ሃሰተኛ ብር እጅ ከፍንጅ ተይዘው ምርመራ እየተደረገ እንደሆነ ፖሊስ ገልጿል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብ/ኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ፡– (@tikvahethiopia)